መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ 52ኛው የሸገር ደርቢ በቡናማዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል
ቅዱስ ጊዮርጊስኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

52ኛው የሸገር ደርቢ በቡናማዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

በሀገሪቱ እግር ኳስ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና 3ለ1 በሆነ ውጤት ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሸነፍ ችለዋል።

እጅግ በርካታ ደጋፊዎች ስታዲየሙን በሞሉበት እና የቀድሞው የሁለቱ ክለብ ተጫዋቾች የወዳጅነት ጨዋታን ካደረጉ በኋላ በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ዳንኤል ይታገሱ በተመራው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ጎሎችን ያስመለከተን ነበር። 24ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር ሔኖክ ዮሐንስ ወደ ሳጥን ያሻማውን ኳስ ሀብታሙ ጉልላት ተቆጣጥሮ የቡናማዎቹ ተከላካዮች ስህተት ታክሎበት ፍፁም ጥላሁን አራተኛ ተከታታይ ጎሉን በማስቆጠር ፈረሰኞቹን ቀዳሚ አድርጓል። ጨዋታው ቀጥሎ አጋማሹ በዚህ ውጤት ይገባደዳል ተብሎ ሲጠበቅ በተሰጠው ጭማሪ ደቂቃ 45+3 ላይ ከግራ ሳጥን መስመሩ ጠርዝ ላይ አምበሉ ራምኬል ጀምስ የሰጠውን ኳስ የያአብስራ ጎሳዬ ስህተት ታክሎበት ኦካይ ጁል ቡናማዎቹን 1ለ1 ማድረግ የቻለች ጎል መረቡ ላይ አሳርፏል።

ብዙም የጨዋታ ግለቱ ከፍ አይበል እንጂ በደጋፊዎች ህብረ ዝማሬ ደምቆ ቡናማዎቹን መጠነኛ ማነቃቃት ውስጥ ከቶ የተመለሰው ሁለተኛው አጋማሽ 53ኛው ደቂቃ ፉአድ ኢብራሂም ከራሱ ሜዳ በረጀሰሙ የላካትን ኳስ ናይጄሪያዊው አጥቂ አቡበከር አዳሙ ከብሩክ ታረቀኝ ጋር ታግሎ ወደ ኋላ በግንባር ጨርፎ የሰጠውን ኳስ ቢኒያም ጌታቸው በቀላሉ ኢትዮጵያ ቡናን መሪ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር 66ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ዲቫይን ዋቹኩዋ ከማዕዘን አሻምቶ በንክኪ ኳስን ያገኘው ዘላለም አባተ ተጨማሪ ጎል በማከል ጨዋታው በመጨረሻም በኢትዮጵያ ቡና 3ለ1 አሸናፊነት ተቋጭቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...