መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ
ሀዋሳ ከተማወላይታ ድቻየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ቅድመ-ዕይታ

የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ | ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ የሚደረጉ ሲሆን ሰባት ጨዋታዎች ነገ (ረቡዕ) ሲደረጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሀሙስ የሚደረግ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።

የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ጥር 20/2012
የጨዋታው ሰአት: 9:00 ሰአት
የጨዋታው አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ዮናስ ካሳሁን
የጨዋታ ቦታ: ሀዋሳ ሰውሰራሽ ሜዳ

በ10ኛ ሳምንት ጨዋታ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በአዲስ አዳጊው ሰበታ ከተማ በ2-1 ተሸንፈው የተመለሱት ሀዋሳ ከተማዎች ባንፃሩ የፕሪምየር ሊጉም መሪው መቐለ 70እንድርታን በሜዳው አስተናግዶ 1-0 ያሸነፈውን ወላይታ ድቻን በ11ኛው ሳምንት በሜዳቸው ያስተናግዳሉ።
ወጥ የሆነ አቋም የማይታይበት ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ካስተናገዳቸው ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ሽንፈትን ያስተናገደ ሲሆን በነገውም ጨዋታ በሜዳቸው እንደመጫወቱ መጠን ለማሸነፍ የተሻለ እድል ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል። ጥሩ ወቅታዊ አቋም ላይ የሚገኘው ብሩክ በየነ ከመስመር የሚላኩ ኳስች በመጠቀም የሀዋሳ ግብ የማግባት ምርጫ ሊሆን እንደሚችል ሲጠበቅ ለወላይታ ድቻ ተከላካዮች የቤት ስራ እንደሚሆንም ይገመታል ።

ይሁን እንጂ ከሽስሑል ሽረ 2-0 ከተሸነፉበት ጨዋታ በኳላ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን አሰናብተው የሊጉን መሪ መቐለ 70 እንድርታን በመርታት ተከታታይ ድል ያስመዘገቡት የጦና ንቦች። ካላቸው ወቅታዊ አቋም አንፃር በቀላሉ እጅ ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። በምክትል አሰልጣኙ ሳሙኤል ደቻሳ የሚመራው ወላይታ ድቻ በተከታታይ ያጣቸውን ነጥቦች ለማሳካት በከፍተኛ መነቃቃት ሀዋሳን ረተው ከሊጉ ግርጌ ከፍ ለማለት ከባዬ ገዛኸኝ ጋር ጥሩ ጥምረት የሚያሳዩት ፈጣን የሚባሉ የመስመር ተጫዋቾች ያሉባቸው ድቻዎች ማጥቃት መሰረት ያደረገ አጨዋወት ይዘው እንደሚጫወቱ ይገመታል። ከጉዳቱ አገግሞ በ10ኛው ሳምንት ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ግብ ማስቆጠር የቻለው ወጣቱ አጥቂ መስፍን ታፈሰ ዳግመኛ የተጎዳ ቢሆንም በዛሬው እለት ልምምድ የሰራ ሲሆኝ ለነገው ጨዋታ የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ ነው። በወላይታ ድቻ በኩል ነጋሽ ታደሰ ከጉዳቱ ሲያገግም ይህ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የተሰማ ጉዳትም ሆነ ቅጣት የለም።

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ድቻ በ2006 ወደ ሊጉ ከመጣ በኳላ በ12 ጊዜ በእርስ በእርስ ግንኙነታቸው ወላይታ ድቻ 6ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ 2 ጊዜ ብቻ ሲያሸንፉ በ4ቱ አቻ ተለያይተዋል።በዚሁም ድቻ 13፤ሀዋሳዎች 8 ያህል ጎል ማስቆጠር ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...