ሎዛ በቃለመጠቁ ላይ ከአስተዳደጓ ጀምሮ ስለእግርኳስ ህይወቷን በስፋት የህይወት ልምዷን ያጋራች ሲሆን ኢትዮጵያን በሴቶች አፍሪቃ ዋንጫ ተሳታፊ ማድረግ ህልሟ እንደሆነም ጨምራ ገልፃለች።
በተጨማሪም በቀጣዮ አመት በአውሮፓ ቻምፕዮንስ ሊግ አሁን እየተጫወተችበት ካለው የማልታው ቢርክርካራ ክለብ ጋር ተሳታፊ ለመሆን ጠንክራ እየሰራች እንደሆነ ገልፃ የእርሷ የአውሮፓ ጉዞ የእግርኳስ መልማዮችን ወደኢትዮጵያ እንዲያማትሩ ሊያደርግ እንደሚችል ገልፃ በርትታ በመስራት ትልልቅ ክለቦች ኢትዮጵያዊን ተጫዋቾች ምርጫቸው እንዲያደርጉ እንደምትጥር አያይዟ ገልፃለች።
ድህረገፁ ሎዛን እንግሊዝ ሃገር መጫወት ትፈልግ እንደሆነ ጠይቋት፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሱፐር ሊጉን በቅርበት እየተከታተለችው እንደሆነ ገልፃ ለሊጉ የሚመጥን አቅም እንዳላትም ጠቅሳለች።
- ማሰታውቂያ -
ብራዝላዊቷን ኮከብ ማርታን እንደ አርአያ እንደምትመለከት የገለፀችው ሎዛ ምክንያቷን በስፋት አስረድታ ማርታ እግርኳስን መጫወታ ከማቆሟ በፊት አብራት መጫወት እንደምትፈልግ ገለፃለች።
መሉውን ቃለመጠይቅ በሚከተለው ማስፈንጠርያ በመጠቀም ያንብቡት: