መነሻ ገጽ Uncategorized የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ ተመረቀ
Uncategorized

የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ ተመረቀ

አጋራ
አጋራ

 

 

የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የካፍ ፕሬዚዳንት ኢሳ ሃያቱ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የስፖርት ሰዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መንግስት በስፖርቱ ዘርፍ ስኬት ለማስመዝገብ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ አካዳሚው አስተዋፅኦው የጎላ ይሆናል ብለዋል፡፡

17308762_1286195048084511_1850735535775318093_n

የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ስታዲየሞች በመንግስት እየተገነቡ ሲሆን፥ የግል ተቋማትም በስፖርቱ ዘርፍ አብረው መስራት ከፈለጉ በሩ ክፍት መሆኑን አንስተዋል አቶ ደመቀ፡፡

የካፍ ፕሬዚዳንት ኢሳ ሃያቱ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እግር ኳስን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት የአካዳሚው መገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ነው የገለፁት፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ፥ አካዳሚውን ያስገነባው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በሀገሪቱ ላለፉት ዓመታት የእግር ኳስ አምባሳደር መሆኑን አንስተው፥ አካዳሚው ኢትዮጵያ በቀጣይ ክህሎት ያላቸው የእግርኳስ ተጫዋቾችን እንድታገኝ ያስችላታል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እንሰራለን ያሉት ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል ናቸው፡፡

በሀገሪቱ ፈር ቀዳጅ የሆነውን የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዳሚ የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ በቅርስነት ሊጠበቅ እንደሚገባውም ነው አቶ አብነት ያሳሰቡት፡፡

ዛሬ የተመረቀው የይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች የስፖርት አካዳሚ በ70 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን፥ ሁለት እግር ኳስ ሜዳዎችና ጅምናዚየምን አካቶ የተሰራ ነው፡፡

በ24 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ አካዳሚ፥ በአውሮፓ በእግር ኳስ አካዳሚ ስኬታማ በሆነቺው የሆላንድ ባለሙያዎች የሚተዳደር ይሆናል፡፡

በውስጡም የእንግዳ መቀበያ፣ የጤና ማዕከላት፣ እና የመመገቢያ ኣዳራሽ ተሰርቶለታል፡፡

አካዳሚው ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምርም በአንድ ጊዜ ብቻ ከ80 እስከ 100 የሚሆኑ ወጣቶችን ማስተናገድ ይችላል፡፡

አካዳሚው ራሱን እስከሚችል ድረስም ሞሃ፣ ደርባ እና ሆራይዘን ፕላንቴሽን በጋራ 50 በመቶውን እንዲሁም ቢ ጂ አይ

ኢትዮጵያ 50 በመቶ ወጭውን በመሸፈን ድጋፍ ያደርጉለታል ተብሏል፡፡

አካዳሚው ሥራውን ሲጀምርም በየዓመቱ 10 ሚሊየን ብር ያስፈልገዋል ነው የተባለው፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...