የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ተወዳጇ ቤስት ስፖርት መፅሔት እንደተለመደው ሁሉ ነገ ቅዳሜም የየካቲት ወር እትሟ ከምርጥ ዘገባዎቿ ጋር በገበያ ላይ ይውላል፤ ቤስት ስፖርት መፅሔት ነገ ስትቀርብሎትም ከሀገር ውስጥ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለኤሌክትሪክ ክለብ በአጥቂ ስፍራ ላይ ስለሚጫወተው እና ጎልም እያስቆጠረ ስላለው እንደዚሁም ደግሞ ከኳሱ ውጪም የድግሪ ተመራቂ ስለሆነው ፍፁም ገብረማርያም የእግር ኳስ ሕይወት አስመልክተን ላቀረብንለት ጥያቄ ሰፋ ያለ ምላሹን ሰጥቶናል፤ ከባህር ማዶ ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትዱ አንቶኒዮ ቫሌንስያ በኦልድ ትራድፎርድ እንዴት እንደ አዲስ ሊወለድ እንደቻለ፤ የሄነሪንና የቤርካምፕን ጥምረት ስለተካው የሜሱት ኦዚል እና የአሌክሲስ ሳንቼዝ ጣፋጭ ዘገባዎች፣ የሊቨርፑሉ ደስተኛ ተዋጊ ስለሆነው ሮቤርቶ ፍርሚኖ፣ ዋይኒ ሩኒ በጎል ሪከርድ ስላሸበረቀበት ያማረ የእግር ኳስ ሕይወት እንደዚሁም ደግሞ የሰማያዊዎቹ ቁልፍ ተጨዋች ስለሆነው ኔማኒያ ማቲች የሚወዷቸው ዘገባዎች ቀርቦሎታል፤ እንዳታመልጦት፡፡
የቤስት ስፖርት መፅሔት የነገው የፊት ገፅ ይህን ይመስላል
አስተያየት ይስጡ