መነሻ ገጽ Uncategorized የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።
Uncategorized

የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።

አጋራ
አጋራ

ለ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ እና ከ23ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ማጣሪያ ከማሊ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን 1-1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቆ በመልሱ ጨዋታ የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቷል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ተመጣጣኝ የሚባል ጨዋታ የታየ ሲሆን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ያልተደረገበት ነበር። አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ ከሲሼልስ አቻው ጋር ካደረጋቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች እጅግ ተሽሎ የተገኘ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ተጭኖ መጫወት ችሏል። በመጀመሪያው አጋማሽ ግን ሁለቱም ቡድኖች በመከላከል በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ ታይተዋል። የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ደስታ ዮሐንስ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደግብ የሞከራት እና የማሊው ግብ ጠባቂ የመለሰበት ኳስ በመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠቀስ የሚችል ብቸኛው ጠንካራ ሙከራ ነበር።

ሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ 8ደቂቃዎች በኋላ 53ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ትኩረት ማነስ ተከትሎ የተሰራውን ስህተት በመጠቀም የማሊው ዲያዴ ዲያንካ ግብ አስቆጥሮ የማሊ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።

ከዚህች ግብ መቆጠርም በኋላ ጫና ፈጥረው ለመጫወት የሞከሩት የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ወደ ማሊ አቻቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ለመድረስ ጥረት አድርገዋል። ሱራፌል ዳኛቸውን በአፈወርቅ ኃይሉ የቀየሩት የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጫና ፈጥረው ተጫውተዋል። ይህንንም ተከትሎ 74ኛው ደቂቃ ላይ ተከላካዩ ደስታ ደሙ በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል።

ከአቻ ጎሏም በኋላ በአማኑኤል ገ/ሚካኤል, በአቡበከር ነስሩ እና ከነዓን ማርክነህ አማካኝነት ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም ወደ ግብነት መቀየር ሳይችሉ ቀርተው ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ ማሊ ባማኮ ላይ የሚከናወን ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

FIFA temporarily lifts transfer ban on St. George

Saint George's has had its transfer ban imposed by FIFA temporarily lifted...

Uncategorized

29ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ዳግም ወንድሙ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ክለቡ ከ መቐለ 70 እንደርታ...

Uncategorized

ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም ራሳቸውን አገለሉ

ሀያ አምስት አመታቶችን በዳኝነት ያገለገሉት ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም በይፋ ማቆማቸውን...

Uncategorized

ወልዋሎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋገጠ

በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ወልዋሎ ዓ/ት ዩኒቨርስቲ በመለያ ምት...