መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስ ​የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቲክስ ጉዳዮች ዙሪያ ለስፖርት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስ

​የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቲክስ ጉዳዮች ዙሪያ ለስፖርት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

አጋራ
አጋራ

​የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ሰኔ 6/2009 ዓ. ም. ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሄንግሎ የኢትዮጵያ ትርያል ውድድርና በተዛማጅ የአትሌቲክስ ጉዳዮች ዙሪያ ለስፖርት
ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

 በመግለጫው ላይ የተነሱ
ነጥቦችም፡-
1. ከሰኔ 3 – 4/2009 ዓ.ም በኔዘርላንድ – ሄንግሎ ከተማ ሲካሄድ
በነበረው የኢትዮጵያ ትርያል ውድድር ዙሪያ አስፈለጊነቱ ምንድነው፣
የታዩ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ ነበር፣ ለፌዴሬሽኑ ምን ጠቀሜታ
አላቸው፣ ….
2. ከሰኔ 7 – 11/2009 ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ለ4ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ
ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይካሄዳል፣ በዚህ ውድድር ዙሪያ
አስፈላጊነቱ፣ የተሳታፊ መረጃ፣ …..
በ4ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 31
ቡድኖች በ372 ወንዶችና በ295 ሴቶች በድምሩ በ667 አትሌቶች
ተወዳዳሪ ይሆናሉ፡፡
4ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክሰ ሻምፒዮና ከሰኔ
7-11/2009ዓ.ም. በአሰላ ግሪን ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
ሻምፒዮናው የሚከተሉትን ዓላማ አድርጎ ይካሄዳል፤
• በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮችና በክለቦች ለሚገኙ ታዳጊ
አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤
• ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤
• ኢትዮጵያን ወክለው በአህጉርና አለም አቀፍ ውድድሮች የሚሳተፉ
ታዳጊ አትሌቶችን ለማፍራት፤
• ከጁላይ 12-16/2017 በኬኒያ ናይሮቢ በሚካሄደው 10ኛው
የአለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው
የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለመምረጥ፤
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሁሉም አትሌቲክስ ህብረተሰብ
ሻምፒዮናው በሚካሄድበት ቦታና ጊዜ ተገኝቶ የነገ ተተኪ አትሌቶችን
እንዲያበረታታ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
3. ኬንያ ላይ ስለሚካሄደው 10ኛው የአፍሪካ ታዳጊዎች አትሌቲክስ
ሻምፒዮና መረጃ ባጭሩ፣
ከጁላይ 12-16/2017 በኬኒያ ናይሮቢ በሚካሄደው 10ኛው የአለም
ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው ስለሚወዳደሩ
አትሌቶች፣
4. በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አገራችንን የሚወክሉ የማራቶን
አትሌቶች በመምረጫ መስፈርት ስለመመረጣቸውና እስከ አሁን
ምንም አይነት ቅሬታ ስላለመቅረቡ፣

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስዜናዎች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድጋፍ ለሚስፈልጋቸው አሰልጣኞችና አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

ፌዴሬሽኑ በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ...

ሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስዜናዎች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

• ፌዴሬሽኑ የብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ኮማንደር አትሌት...