የኢትዮጵያ ቡና ሃምሌ 9/2009 የሚደረገው የቡና ቤተሰብ ሩጫ በዛሬው እለት በሂልተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰጠው የክለቡ አመራሮች ፣ የደጋፊው ማህበሩ አመራር ፣ደጋፊዎች እንዲሁም የሚዲያ አካላት በተገኙበት ነበር፡፡

ጋዜጣዊው መግለጫው የተጀመረው የክለቡን መዝሙር በመዘመር ሲሆን በመቀጠልም የክለቡ የቦርድ አመራር የሆኑት አቶ ይስማሸዋ ስዩም ንግግር አድረገዋል፡፡ አቶ ይስማሸዋ በንግግራቸው ስለ ሩጫው ማበራሪያ የሰጡ ሲሆን ፡፡ የሩጫው መነሻው በጀሞ ስልሳ ሰባት ማዞሪያ በለቡ መብራት ሃይል አድርጎ በጀርመን አደባባይ እንዲሁም በጀሞ ሚካኤል አድርጎ የክለቡ ስተዲየም በሚገነባበት ሜዳ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል ፡፡ ይህ የሁለተኛው ዙር የቡና ቤተሰቦች ሩጫ 8 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ሜዳችን በራሳችን በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል ፡፡ሩጫው በአትሌት ሺ አለቃ ደራርቱ ቱሉ የሚጀመር ሲሆን በእለቱም ከፈተኛ መንግስት ባለስልጣንና የመከላከያ የማርሽ ባንድ በተገኙበት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሰታድዬም የመሰረት ድንጋይ የሚጣል ይሆናል ፡፡ስታዲየሙ በጀሞ አከባቢ ከመንግስት በተሰጠ 35 ሺ ስኩዌር ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያርፋል ፡፡ ግንባታውም በ2010 እንደሚጀመር እና በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከ35-45 ሺ መቀመጫዎች እንደሚኖረውና 350 ሚሊዮን ብር ለግንባታው እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ፡፡

የመሮጫው ቲሸርት ከሃሙስ ጀምሮ በክለቡ ፅ/ቤት ና ደጋፊው በተመዘገቡበት ቦታ በመሄድ መውሰድ እንደሚችሉ የተነገረ ሲሆን፡፡ እንዲሁም ከቲሸርቱ ጋር የሩጫ ህግጋት እንደሚሰጡም የትሸርቱ ቀለም አይነት ይፋ ተደርጓል፡፡ በሩጫው እለት የምግብ ና የመጠጥ እንዲሁም አንቡላንስ አገልግሎት እንደተዘጋጀ የፋ ሆኗል ፡፡የሩጫው አዘጋጅም ሲሳይ አድማሴ ፕሮሞሽን እንደሆነ ተገልጧል፡፡
በመቀጠልም የክለቡ የደጋፊዎች ማህበር አመራር አቶ ክፍሌ አማረ ሩጫው ሰላማዊ እንደሚሆን እንተማመናለን ብለው ሯጮች ህግጋቶች እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ከደጋፊዎችና ከሚዲያ አካላት የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በእለቱም የቦርድ አመራርና የደጋፊው ማህበር አመራሮች ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልስ ሰተዋል፡፡
የክለቡ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የአስታዲየም ግንባታ በተመለከተ ግንባታው በእኛው ተጀምሮ በእኛው እንደሚያልቅና ቡና ሃፍቱ ደጋፊው እንደሆነ ተናግረው ሁሉም ደጋፊ የበኩሉን እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አክለውም ለደጋፊው እና ለሩጫው ኮሚቴ ምስጋና አቅረበው ሩጫው በሰለም እንደሚጠናቀቅ ያለቸውን ተስፋ ገልፀው ለደጋፊው 12 ቁጥረ ማሊያ አበርክተዋል፡፡
Source-ethiopia coffee fb page
አስተያየት ይስጡ