መነሻ ገጽ Uncategorized ​የኘሪሜየር ሊጉ መሪዎች ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት መሪነታቸውን እሚያስቀጥሉበት ድል አስመዝግበዋል
Uncategorized

​የኘሪሜየር ሊጉ መሪዎች ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት መሪነታቸውን እሚያስቀጥሉበት ድል አስመዝግበዋል

አጋራ
አጋራ

በ25ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ሲውል በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
አዲስ አበባ ላይ ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፥ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ ደደቢት ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዷል።

dedebit.pngdire-dawa-city-fc
በጨዋታውም ደደቢት ድሬደዋ ከተማን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።
ደደቢትን አሸናፊ ያደረገችውን ጎልም ዳዊት ፍቃዱ በ83ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

George

pic-source የፈረሰኞቹ ገጽ

ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከተማ የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ 9 ሰዓት ላይ በሜዳው ያስተናገደ ሲሆን፥ ጨዋታውም በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ አብዱልከሪም ኒኪማ በ67ኛ ደቂቃ ላይ ብቸኛዋን የቅዱስ ጊዮርጊስ የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል።
በሌላ ጨዋታ ደግሞ በሊጉ የወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከተማ ከ10 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

combank-logofasil kenema
ጨዋታውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ለ1 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ቢኒያም አሰፋ በ4ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና የጨዋታው መደበኛ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪ 90+2 ደቂቃ ላይ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እና ፒተር ንዋድኬ በ86ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ንግድ ባንክን አሸናፊ አድርገዋል። ፋሲል ከነማን ከመሸነፍ ያልታደገችውን ጎል ይስሃቅ መኩሪያ በ24ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
በዚሁ መሠረት 25ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲጠናቀቅ የደረጃ ሰንጠረዡ ከታች ይመልከቱ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...