መነሻ ገጽ U -17 ብሄራዊ ቡድን ​ዘወትር ማክሰኞ በገበያ ላይ በመዋል ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟም 
U -17 ብሄራዊ ቡድንUncategorized

​ዘወትር ማክሰኞ በገበያ ላይ በመዋል ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟም 

አጋራ
አጋራ

ለውድ አንባቢዎቿ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን በሚወዱት መልኩ ይዛላችሁ ትቀርባለች፤ የእኛ እና የእርሶ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ከሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ የምስራቅ አፍሪካን ወክለው የካፍ ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ለመግባት ሰፊ እድልን ስለያዙበት ሁኔታ ዘገባዋን ይዛላችሁ ስትቀርብ ሌሎቹ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን መሪነትን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከተረከበው የአዳማ ከተማው ስኬታማ ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸው ጋር በክለቡና በእራሱ አቋም ዙሪያ ስለሰጠው አስተያየት፣ የጅማ አባቡናው አሰልጣኝ ደረጄ በላይም ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተጫውቶ 1-1 ከተለያየ በኋላ ከክለቡ ጋር ስለተለያየበት እና ስለቡድኑ የሚሰጠው አስተያየት አለ፤ ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ረዳት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝም ከጅማ አባቡና ጋር ከተጫወቱ በኋላ ስለቡድናቸው የሰጠው አስተያየትም አለ፤ ከባህር ማዶ ዘገባዎች ውስጥ ደግሞ በጋቦን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ስላለው የአፍሪካ ዋንጫ፣ የአርሰናል ነፍስ አዳኝ ስለሆነው አሌክሲስ ሳንቼዝ ስለ ማንቸስተር ዩናይትዱ ታሪክ ሰሪ ተጨዋች ዋይን ሩኒ፣ የሊቨርፑል ምልክት ስለሆነው ስቴቨን ጄራርድ በአዲስ የህይወት ምህራፍ ስለመምጣት እና የቼልሲው ዲያጎ ኮስታ ለቡድኑ የውጤታማነት ቁልፍ ሰው ስለመሆኑ ሀትሪክ በሰፊው ልታስኮመኩማችሁ ተዘጋጅታለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ከእነዚህ ዘገባዎቿ በተጨማሪ በመዝናኛ አምዷም የምትወዱት ምርጥ ዘገባዎችም ይኖራታልና፤ እንዳታመልጦት፡፡ የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ገፅ ይህንን ይመስላል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
U -17 ብሄራዊ ቡድንዜናዎች

ዳዊት ካሳው እና ቢኒያም አብርሃ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነዋል

በኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች የሴካፋው ብሔራዊ ቡድን የደመቁት ሁለቱ ተጫዋቾች ወደ አፍሪካ...

Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...