“ሁሌ ማሸነፍ የተለመደበት ፤ መሸነፍ ይቅርታ የሌለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነው…”
“አምናና ካቻምና በተወሰነ መልኩ ድክመቶች ስለነበሩብን ዋንጫውን አጥተናል”
“ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው…ለክለቡ መጫወት በተጨዋችነት ዘመንህ የተሻለ ታሪክ እንድትሰራ ያደርግሃል”
ተወልዶ ያደገው በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ በምትገኘው ጨንቻ ወረዳ ውስጥ ነው ለኳስ ተጨዋች አርአያ የሚሆን መሪ በሌላት በዚህች ወረዳ ግን ምልክት የሆነው እንግዳችን ለተምሣሌትነት ተገኘ……አርባ ምንጭ ከነማና ሲዳማ ቡና በጋራ ለ6 አመታት የዚህን የመሀል ሜዳ ታጋይ ግልጋሎት አግኝተዋል፡፡ ብቃቱን ያዩት ፈረሰኞቹ ደግሞ በ2010 በእጃቸው አገብተውት ዘንድሮ 3ኛ – አመቱን ይዟል የመሀል ሜዳ ታጋዩ ዲኮ…..ዴኮ ሙላለም መስፍን ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ስለ ቅፅል ስሙ፣ እርዳታ መስጠት ስላለው ደስታ፣ ባለፉት 2 አመታት ጊዮርጊስ ስላጣው ዋንጫና ስለ ሲቲ ካፑ፣ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት፣ የውጭ ሀገር ግብ ጠባቂዎች ስለመብዛታቸው፣ ጠንካራ ተፋላሚዬ ነው ስለሚለው ተጨዋች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስለመሆኑና ሌሎች ጉዳዮች ምላሹን ሰጥቷል፡፡
በዮሴፍ ከፈለኝ
ሀትሪክ፡- በጅማ አባጅፋር ለመሸነፋ ችሁ ዋነኛ ምክንያት የምትለው ምንድነው ?ሽንፈቱስ ምን ስሜት ፈጠረብህ…?
ሙሉዓለም፡- ሽንፈቱ በጣም ያማል…ቅርም ብሎናል፤ወደ ጨዋታው ስንመለስ እኛ ተቀዛቅዘን መግባታችን ሳንጫወት እንዳምናሸንፍ አምነን መግባታችን ለሽንፈት ዳርጎናል፡፡ ግብ አካባቢ የተፈጠረው ስህተት ውጤታችንን አበላሽቶብናል፤በቀጣይ ግን ቁጭ ብለን ተነጋጋረን ወደ አሸናፊነት እንደምንመለስ እርግጠኛ ነኝ ፤አብረውን ለነበሩት ተጓዥ ደጋፊዎችና ለመላው የጊዮርጊስ ደጋፊዎች ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡
ሀትሪክ፡- አጥቂው ክፍል ጋር መሳሳት መኖሩስ ዋጋ አላስከፈለም ትላለህ?
ሙሉዓለም፡- …ሳላሀዲን አለመኖሩ የፈጠረው ክፍተት እየታየ ነው፤የጌታነህ ከበደ አቅም እንደወትሮው አለመሆንም ጎድቶናል፤በቀጣይ ጨዋታዎች ግን እንደ ቡድን ተንቀሳቅሰን ለማሸነፍ እንጥራለን፡፡
ሀትሪክ፡- ዳኝነቱስ ጥሩ ነበር?
ሙሉዓለም፡- አዎ ጥሩ ዳኝነት አይቻ ለሁ በዳኛው ላይ ችግር የለብኝም፡፡
ሀትሪክ፡- የቅፅል ስምህ ዴኮ ይባላል… የፖርቱጋሉን ተጨዋች ስያሜ ተሰጥቶሃል ማለት ነው…. ስሙን ትወደዋለህ?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ/ በጣም ነው የምወደው… በርግጥ ዴኮ የሚለውን ስም ያገኘሁት ከዴኮ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን እቤት የምጠራበት ስም ዲኮ.. ነው በጋሞኛ ደግሞ ዲኮ ማለት ካለህ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ስም ተይዞ የሰፈር ልጆች ኳስ ስጫወት አይተው ዴኮ ወደሚለው አጠጋጉና ዲኮ.. ዴኮ በሚለው ተቀይሮ ቀረ….. ይሄ ነው ታሪኩ፡፡
ሀትሪክ፡- ስለዚህ ዲኮም ሆነ ዴኮ ተመችተውኛል እያልክ ነው?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ/ ሁለቱንም እወዳቸ ዋለው
ሀትሪክ፡-በከፍተኛ ሊግ የሚወዳደር ጨንቻ የተሰኘ ክለብ አለ.. የትውልድ ከተማህክለብ እንደመሆኑ ትደግፋቸዋለህ?
ሙሉዓለም፡- አዎ ሁለተኛው ሊግ ላይ ጋሞ ጨንቻ የሚባል ክለብ አለ፡፡ እኔን አይተው የወጡ ተጨዋቾች ያሉበት ክለብ ነው…. ታናሽ ወንድሜም የቡድኑ ተሰላፊ ነው ከነርሱ ጋር ቀን በቀን እንገናኛለን በቅርቡ ሻሸመኔላይ ጨዋታቸውን ሄጄ አይቻለሁ፡፡
በማቴሪያል ልደግፋቸው ዝግጅት ላይ ነኝ ማሊያዎችና አንዳንድ ለቡድኑ የሚጠቅሙ ማቴሪያሎችን ግዢ እያጠናቀኩ ነው በቅርቡ ለክለቡ አስረክባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- እርዳታ ለማድረግ መነሳትህ የፈጠረብህ የደስታ ስሜት የለም?
ሙሉዓለም፡- በጣም ተደስቻለው…. እድሉን ማግኘቴ አስደስቶኛል እርዳታ መስጠት ያረካል ከዚያ አካባቢ የወጣ ተጨዋች ስለሌለ ምናልባት የመጀመሪያው ሳልሆን አልቀርም ባይ ነኝ አካባቢው ብዙ አቅም እያለው በርቀቱ ብቻ ብዙ ትኩረት አላገኘም፡፡ ከፍተኛ ሊግ ላይ እንደመገኘቱ ግን ልጆቹን ማገዝ ማበረታት በመቻሌ ደስ ብሎኛል…..ወንድሜ፣ አብረውኝ ያደጉና አብረውኝ የተማሩ ተጨዋቾች አሉበትና እነርሱን ከመደገፍ የበለጠ ደስታ የለም፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ኳሱ ስትገባ ተምሣሌት ነበረህ?
ሙሉዓለም፡- ምንም አልነበረም.. በተወለ ድኩበት አካባቢ ሞዴል የነበረ ሰው የለም፡፡ ከአካባቢው አንፃር በተጨዋችነት የወጣ የለም እኔም የወጣሁት በአጋጣሚ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ምን ማለት ነው በአጋጣሚ?
ሙሉዓለም፡- ኳስ ተጨዋች ለመሆን አላቀድኩም አካባቢዬም እንዳቅድ አላደረገኝም አመታዊ የወረዳዎች ውድድር ነበር እዚያ ላይ ስጫወት ነው የታየሁት አባቴ ኳስ ድሮ ይጫወት ስለነበር ጫማና ኳስይገዛልኝ ነበር… ብዙ ሜዳዎች አሉ ወረዳው ሙሉ አረንጓዴ ነው 2002 ላይ በነበረ የወረዳ ጨዋታ ላይ ስጫወት ጎን ለጎን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አመጣሁና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ገባው ያኔ ለምን እየተጫወትክ አትማርም ብለውቡድኑን ተቀላቀልኩ.. ይሄ ነው የኳሱ መነሻ፡፡
ሀትሪክ፡- የዩኒቨርሲቲን ትምህርት ጨርሰህ ተመረቅክ?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ/ አዎ ጨርሼ በሂስትሪ ኤንድ ሄሪቴጅ ማኔጅመት ተመርቄያለሁ፡፡ ነገር ግንበትምህርቱ አልቀጠልኩም ውስጤ ግን ሃሳቡ አለ መማር እፈልጋለው ነገርግንከኳሱ ጋር ስለሚጋጭአልቻልኩም በቅርቡ የምቀጥል ይመስለኛል፡፡በተልዕኮ መማር አልፈለኩትም ጊዜ ወስጄ መማሬ ግን የግድ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የተማረ ተጨዋች ማግኘት ብዙም ይከብዳልና ሁኔታውን እንዴት ትገልፀዋለህ…?
ሙሉዓለም፡- በአጋጣሚ ነው ኳስ ተጨዋች የሆንኩት ብዬሃለው በአካባቢም ተጫውቶ የመጣ የለምና ቤተሰቤም ትምህርቱ ላይ እንድናተኩር ነው የሚያስገድደው አባቴ በዚህ ላይ ጠንካራ አቋም ነበረው፡፡ በኳሱ እንድጫወት ሲያበረታታኝ ለስሜት እንጂ እዚህ ይደርሳል ብሎ አልነበረምና ዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ኳስ ተጨዋች የመሆን እድልም ማግኘቴ አስደስቶኛል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቃድ ስለሆነ ነው አሁን ያለሁበት ቦታ ያለሁበት፡፡ ቤተሰቦቼ አሁን በደንብ ይደግፉኛል በዚህም ተደስቻለው፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን የያዘው አቋም ለዋንጫው ያስተማምናል ማለት ይቻላል?
ሙሉዓለም፡- አሁን ላይ ምንም መናገር ከባድ ነው… አሁን ማለት የሚቻለው ጥሩ ተፎካካሪ ለመሆን የምንችለው እንጥራለን ነው እንጂ ለዋንጫ ነው አይደለም የሚለው ከበድ ይላል፡፡
ሀትሪክ፡- ሁለት አመቱ ጊዮርጊስ ከዋንጫ የራቀበት ነውና ለምን መጣሁ ሲዳማ ቡና ብቀርስ የሚል ስሜት አልተሰማህም?
ሙሉዓለም፡- ለምን መጣሁ የሚል ስሜትተሰምቶኝ ያውቃል…. ለጊዮርጊስ የፈረምኩት ዋንጫ ፈልጌ ነው፡፡ በአፍሪካ መድረኮችም ለክለቡ የምችለው አደርጋለው ብዬ አስቤ ነበር ግን አልተሳካም የሀገር ውስጥ ዋንጫ በጊዮርጊስ ቤት ባልተለመደ መልኩ በተከታታይ 2 አመት ታጥቷል ያ ደግሞ በኔ ጊዜ መሆኑ ቅር ያሰኛልና ምነው ባልመጣው ብዬ አስቤ አውቃለው… በተቃራኒው በቀጣይ አመቶቼ ዋንጫ የማንሣት ተስፋ ይዤ ተፅናንቻለው፡፡ በተለይ የመጀመሪያው አመቴ ላይ ከጅማ አባጅፋር ጋር በጎል ተበልጠን ነው ዋንጫውን ያጣነው ጥሩ ስሜት እንዳይሰማኝም አድርጓል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ዋንጫ ይኖራል ምናልባትከሌለ ደግሞ ክፍያው መፅናኛ ይሆናል የሚሉ አሉ…. እውነት ነው?
ሙሉዓለም፡- አሁንኮ ጥሩ ክፍያ የትም ይገኛል፡፡ የተሻለም ደመወዝ ልታገኝ ትችላለህ.. ዋናው ለኔ ክፍያው አይደለም ታሪክ ሰርቼ የማለፍ ህልም አለኝ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው…ለክለቡ መጫወት በተመለከተ
ጨዋችነት ዘመንህ የተሻለ ታሪክ እንድትሰራ ያደርግሃል ከዋንጫ አልፎ ሌሎች ስኬቶችን የምታስበው በጊዮርጊስ ማሊያ ነውና የኔ ሃሣብ ብሩ ሳይሆን ታሪኩ ነው ገንዘብ ብቻ ያረካል ብዬ አላምንም… ብዙ ታሪክ የሰራበርካታ ደጋፊ ያለው ክለብ እንደመሆኑ በዚህ ቡድን ውስጥ መገኘቴ ነው ርካታ የሚሰጠኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ሁለቱን አመት በተገቢው መንገድ ተሸንፈን ዋንጫ አላጣንም የሚሉ ደጋፊዎች አሉ.. አንተስ?
ሙሉዓለም፡- እንዲህ ብዬ ራሴን አልሸውድም፡፡ ምክንያቱም እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ መታገላችን ከኛ የሚጠበቅ አይደለም እዚያ ድረስ መድረስ አልነበረብንም፡፡ የካቻምናውን ዋንጫ ጨዋታዎች እየቀሩ ማሸነፍ ነበረብን፡፡ ይሄ ላለመደረጉ ሰበብ መደርደር አልሻም የአምናውም ቢሆን እድሉ ነበረን ነገር ግን የሌሎቹን ክለቦች ውጤት መጠበቅ ነበረብን በኛ ማሸነፍ ላይ የተመሰረተ አልነበረም፡፡ የሌሎችን ውጤት እየጠበቁ ሰበብ መደርደር አልሻም የተፈጠረው ችግር እያለ ሌሎች ክለቦችም ከላያችን ነበሩ.. ይሄ ጊዮርጊስን አይመጥንም በቃ አምናና ካቻምና በተወሰነ መልኩ ድክመቶች ስለነበሩብን ዋንጫ አጥተናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የአዲስ አበባ ዋንጫ አሸናፊ መሆናችሁ… ምን ያሳየህ ነገር አለ?
ሙሉዓለም፡- ቡድናችን ሲቲ ካፑ ላይ ጠንካራ ነገር ያሳየው የአጥቂዎቻችን ተሟልቶ መገኘትና ለቡድኑ ግልጋሎት መስጠታቸው ነው ሳላሀዲን ጥሩ ነበር ጌታነህ ገባ ወጣ እያለ ክለቡን ያገለግል ነበር… ይሄ በደንብ ጠቅሞናል አምና ካቻምና የአጥቂው ክፍላችን ሳስቶ ነበር ሲቲ ካፑ ላይ ግን ችግሩ በመቀረፉ ከጨዋታ ጨዋታ እየሻሻልን ጠንክረን ዋንጫ ወስደናል ይሄ ከቀጠለ ጥሩ ውጤት ይመጣል ብዬ አምናለው፡፡
አሁን ግን ሳላሀዲን መጎዳቱ ይጎዳናል…. ቡድኑ ውስጥ ገብቶ ሲጫወት የሚኖረን በራስ መተማመን ልዩ ነው አለመኖሩይጎዳናል ነገር ግን ወደ ጤንነቱ እየተመለሰ በመሆኑ ቡድናችን ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር ተመጣጣኝ ነው ማለት ይቻላል?
ሙሉዓለም፡- አዎ ከዚህ በፊት ከነበሩት የዘንድሮው ውድድር ተመጣጣኝነት አለው ብዬ አስባለው፡፡ ሁሉም ቡድኖች ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን አካተዋል.. ሁሉም በፋይናንስም ተፎካክሮ ራሱን አጠናክሯል…..በዘንድሮው ውድድር ከዚህ በፊት ከነበሩት የተሻለ ፉክክር እጠብቃለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የስፖርታዊ ጨዋነት መከበር ላይ ምን የምትለው ነገር አለ?
ሙሉዓለም፡- ቶሎ ባላመሰግን ደስ ይለኛል ነገር ነገር ግን እንደ ጀማሮ በጣም ተደስቻለው…..ብዙዎች ለኳስ ያላቸውን ደካማ አስተሳሰብ የቀየረ ይመስለኛል ሠላሙ ተመልሷል፡፡ ባህርዳርላይ የታየው፣ በአዲስ አበባ ዋንጫ የጊዮርጊስና ቡና ደጋፊዎች ያሳዩት ፍቅር በወላይታ ድቻና በሲዳማ ቡና መሀል ሠላም መፈጠሩን ካየን መልካም ነገር እንዲታየንያደርጋል፡፡በዚህ የሚቀጥልከሆነ እንደ አጀማመሩ ፍፃሜው በሠላም ይጠናቀቃል ብዬ አምናለው፡፡ ሰላሙ ብዙ ደጋፊዎችን በተለይ ከሜዳ የራቁትን ወደ ሜዳ ይመልሳል ብዬ አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ15ቱ ክለቦች የሚለየው በምን ይመልሃል?
ሙሉዓለም፡- ሌላ ቡድን ውስጥ ሆነህ ብትሸነፍ ምንም ችግር የለውም….. ከሜዳ ውጪ ነው ወይም 1ለ0 ነው ተብሎ ለቀጣዩ ተዘጋጅ ተብሎ ይታለፋል…. ጊዮርጊስ ጋር ግን ምንም ሁን ምን የግድ ማሸነፍ አለብህ፡፡ ጥሩ ሆነህ ተሸነፍክ ተብሎ የሚያልፍህ የለም፡፡ ሁሌ ማሸነፍ የተለመደበት መሸነፍ ይቅርታ የሌለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነው….. ሌሎቹ መሸፍ አይወዱም ግን ያን ያህል አይጋነንም ያለው ልዩነት ይሄ ነው፤ ደጋፊው ሁሌም ከቡድኑ ጋር አለ ቡድኑን ከልቡ ይወዳል ይሄም ልዩነቱ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- ሜዳ ስትገባ ታዲያ በጫና ውስጥ ሆነህ ነው?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ/ በርግጥ የመጀመሪያው አመት የተወሰነ ከበድ ብሎኝ ነበር ከዚያ በኋላ ግን ጫና ውስጥ ከመግባት ይልቅ በርትቼ ሰርቼ ያለኝን ነገር አውጥቻለው.. አሁን ጫና ውስጥም አይደለሁም አሁን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፡፡ ራሴን ለጨዋታ ዝግጁ አድርጌ የሚቻለኝን ለማድረግ ነው የምጥረው…..የደጋፊው ጫና አሁን የለብኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ያንተ ጥሩ መሆን የቡድኑን አቋም ይጨምራል ጥሩ ካልሆንክ ግን ቡድኑ ይወርዳልና.. የቡድኑንጉሮሮ የያዝክ አይምስልህም?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ በሳቅ/ እንደዚያ ለማለት እቸገራለው፡፡ ነገር ግን የምችለውን ለማድረግ ወስኜ ነው ወደ ሜዳ የምገባው…. ሁሌም ጥሩ መሆን አይቻልም ቡድኑ በተቃራኒው ክለብ ሲበለጥና ደካማ ሲሆን በተጋጣሚህ የመበለጥ እድል ይኖራል.. በርግጥ ጥሩ ስለሆንክ ብቻ ቡድኑ ጥሩ አይሆንም እኔ መጥፎ አቋም አሳይቼ ቡድኑ ጥሩ የሆነበት ጊዜም አለ የቡድኔን ጉሮሮ የያዝኩ አይመስለኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ትዝ የሚልህ ባንተ ብቃት ቡድኑ ውጤት ይዞ የወጣበት ግጥሚያ አለ?
ሙሉዓለም፡- እንደዚህ አይነት ልዩነቶች ብዙ ጊዜ ግብ ጠባቂ ወይም ተከላካይ ጋር ነው የሚጎላው….ብዙ ጨዋታዎች ላይ ቡድኔን ከመጎዳት መጥቀሜ ነው የሚሰማኝ…. ጓደኞቼ በርግጥ ያወሩኛል ልዩ ነበርክ ይላሉ…
ሀትሪክ፡- የቀድሞ ክለብህ ሲዳማ ቡና ናፈቀህ?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ በሳቅ/ መናፈቁማ አይቀርም ይናፍቀኛል…. የታየሁበት አሪፍ አሪፍ ጊዜ ያሳለፍኩበት ክለቤ ነውና መናፈቁ አይቀርም፡፡
ሀትሪክ፡- የውጪ ዜጎች የግብ ጠባቂ ዎች ቦታ በብዛት መያዛቸው የሀገሪቱን እግር ኳስ አይጎዳም?
ሙሉዓለም፡- ይጎዳል እንጂ… ምንም ጥያቄ የለውም ያው መታረም አለበት በብዙ መድረኮችና መንገዶች የተነሳ ችግር ይመስለኛልና ብሔራዊ ቡድኑ ላይ የሚፈጠ ረውን ተፅዕኖ ለማስወገድ ሁሉም መጣር አለበት፡፡

ሀትሪክ፡- እስካሁኑ ጨዋታዎች የዳኝነ ቱን ነገር እንዴት አየኸው?
ሙሉዓለም፡- የእስካሁኑ ጉዞ አሪፍ የሚባል ነው በኔ እይታ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም… በነገራችን ላይ በባህሪዬ ዳኞችን ማየት ካርድ ሲመዙም መነጋገር አልፈልግም አልነካካም.. ሊሳሳቱ ይችላሉ ብዬ ነው የማልፈው.. በእስካሁኑ ጉዞ ግን ቅሬታ የማነሳበት ዳኝነት አላየሁም፡፡
ሀትሪክ፡- በቦታህ አብሬው ብጫወት የምትለው ማንን ነው?
ሙሉዓለም፡- መስዑድ መሀመድ ጋር ብጫወትብዬ አስባለው በብሔራዊ ደረጃ ሩዋንዳ ላይ አብረን ተጫውተናል ጥሩ ነበርን 2 ጨዋታዎች ላይ ለጋራ አላማ ተፋልመናል.. በክለብ ደረጃ አብሬው ብጫወት ደስ ይለኛል ከዚያ ውጪ ከአስራት መገርሳ ጋርም መጫወት ያስደስተኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ከተፋለምካቸው ተጨዋቾች በቦታህ ጠንካራ ተፋላሚህ የነበረው ማነው?
ሙሉዓለም፡- ይሄን ለማስወገድ ነው መስኡድን ያልኩት…. አማካይ እንደመሆኑ ከጀርባ እየሆነ አስቸግሮኛል በጣም ታክቲካል ነው ቦታውን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃልና አስቸግሮኛል እርሱን ለማግኘት ብዙ ጊዜ እቸገራለው እርሱን ከጀርባዬ እንዳይሆን ፍለጋ ላይ ነው ማተኩረው… ከፊትህ ከሆነ ቀላል ነው ከተከላካዮችና ከኔ መሀል ቆሞ ስለሚጠብቅ በጣም ያስቸግራልና.. እርሱን ነው አብሬው ብጫወት የምለው.. በቦታዬም የተቸገርኩት በርሱ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በቦታህ ያንተ ምርጥ ማነው?
ሙሉዓለም፡- በደንብ ያየሁትና የማውቀው የአርሴናሉ ፓትሪክ ቪየራን ነው…..
ሀትሪክ፡-በክለብ ደረጃ የማን ደጋፊ ነህ?
ሙሉዓለም፡- ከስፔን ባርሴሎና ነኝ እንግሊዝ ውስጥ ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ተቀይሬያለሁ፡፡ አርሰናል ነበርኩ ወደ ሊቨርፑል ፊቴን አዙሬያለው ይሄ ከሆነ 4 ወይም 5 አመትአልፎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ብዙዎች ከሊቨርፑል ነው ወደ አርሰናል የሚሄዱት… የአንተ እንዴት ተለየ.. ምኑ ነው የሳበህ?
ሙሉዓለም፡- እየተጫወተ ያለበት መንገድ በጣም
የሚስብ ነው ፕሬሲንጉ.. ያላቸው ታጋይነት.. ጨዋታ ለማሸነፍ የሚያደርጉት ፍልሚያ በተለይ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ቡድኑን የሚያነሳሳበት መንገድ ስቦኛል ቡድኑ በፍላጎትና አንድነት ጥሩ ቡድን በመሆኑ እንድደግፋቸው አድርጎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ሜሲ….ሮናልዶ…?
ሙሉዓለም፡- ሊዮኔል ሜሲ ምርጫዬ ነው…. ነገር ግን ሮናልዶም ልዩ ነው….ባለፈው ሳምንት በቴስታ ያስቆጠረውን ግብ ስታይ አለማድነቅ አይቻልም.. በአለም ላይ ከሚጠሩት ልዩ ተጨዋቾች መሀል አንዱ ነው ለዚህ ነው ባሎን ደኦርን 5 ጊዜ የወሰደው.. ሜሲን ሳደንቅ ሮናልዶን አሳንሼ አይደለም… ትላልቅ ኳሊቲዎች አሉት የቴስታ ግቡ ደግሞ አንዱ ብቃቱ ነውና እንድገረምበት አድርጎኛል፡፡

ሀትሪክ፡- እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለሀገርህ ምን ትመኛለህ?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ/ ለኢትዮጵያ… ሰሞኑን ወደ ህዋ እንደመጠቀችው ሳተላይት.. በጣም ከፍ ብለን የምንታይበት ወደቀደመው ከፍታችን የምንወጣበት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አንድ የምንሆንበት ጊዜ እመኛለሁ፡፡ ዘር ጎጥ ሃይማኖት ሳይከፋፍለን አንድ ሆነን ዘር ብሔር ሃይማኖት ወደማንቆጥርበት ዘር ጎጥ ሃይማኖት ሳይከፋፍለን አንድ ሆነን ዘር ብሔር ሃይማኖት ወደማንቆጥርበት ዘመን እንድንመለስ እመኛለሁ
ሀትሪክ፡- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሠላም ኖቤል ሲሸለሙ ምን ተሰማህ?
ሙሉዓለም፡- በጣም ተደስቻለሁ የሀገርን ምስል ያስተካክላል ይሄ የሠላም ባሎን ደኦር ነው ብዬዋለው እንደ ሀገር ያስደስታል፡፡
ሀትሪክ፡- ትዳር መሰረትክ.. ፍቅረኛ አለችህ.. ወይስ ነፃ ነህ…?
ሙሉዓለም፡- ገና ነኝ
ሀትሪክ፡- ገና ነኝ… ምን ማለት ነው? ብቸኛ ነኝ እያልክ ነው?
ሙሉዓለም፡- /ሳቅ በሳቅ/ የፍቅር ጓደኛ አለችኝ ይሄ አይበቃም… /ሳቅ/
ሀትሪክ፡- የምታመሰግነው ካለ…?
ሙሉዓለም፡- ማመስገን ላልከው አለማመስገን ይሻላል አንዳንዱን አመሰግነህ ሌላው ስትረሣ እኔን አላመሰገነኝም ብሎ ስለሚከፋ ማለት የምፈልገው እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከኔ ጎን ሆነው ድጋፋቸውን ለሰጡኝ በሙሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ማለት እፈልጋለሁ፡፡

አስተያየት ይስጡ