ከነዓን ማርክነህ በኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ቆይታው
ጥሩ ብቃቱን በሜዳ ላይ በማሳየት መልካም
የሚባል ጊዜን ከክለቡ አዳማ ከነማ ጋር
አሳልፏል፤ በውድድር ዘመኑም ላይ የወቅታዊ
አቋሙን ጥሩ መሆን ተከትሎም ብዙዎቹ
የስፖርት አፍቃሪዎች ከፍተኛ አድናቆትን
ሰጥተውትም አልፈዋል፤ ይሄ ተጨዋች
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከተመረጡት
ውስጥም አንዱ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ
ከሰርቢያው ክለብ ባገኘው የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ዕድል ወደ ቤልግሬድ ተጉዞ
የሙከራን ወቅት ቢያሳልፍም ከሄደበት
የአጭር ጊዜ አንፃር ግን የፕሮፌሽናል
ተጨዋች የመሆን ምኞቱ ለጊዜው
እንዳልተሳካለትና በቀጣይ ጊዜ በሚያደርገው
የሙከራ እድል ግን እልሙ እንደሚሳካለት
ከስፍራው በተመለሰበት ወቅት ለሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፤
የአዳማ ከነማው ከነዓን በሰርቢያ ቆይታው
ስላደረገው የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
የሙከራ እድልና ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች
ዙሪያ አጠር ባለ መልኩ አናግረነው የሰጠንን
ምላሽ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ሙከራን በሰርቢያ ካደረግክ በኋላ ወደ ሀገርህ
ተመልሰሃል፤ በቅድሚያ እንኳን ደህና
መጣህ? የሙከራው ቆይታ ምን ይመስላል?
ከነዓን፡– በመጀመሪያ እናንተም እንኳን
ደህና ቆያችሁኝ፤ ወደ ሰርቢያ ተጉዤ
ያደረግኩት የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ሙከራ
ምንም እንኳን የመሞከር እድሉ ተሰጥቶኝ
እዛ ገብቶ ለመጫወት የሚያስችለኝን ደረጃ
ለማግኘት ባልችልም በቆይታዬ ግን ጥሩ
ትምህርትንና ልምድን በማግኘት ለቀጣዩ ጊዜ
የሙከራው ዕድል ብዙ ያወቅኳቸው ነገሮች
ስላሉ ቆይታዬን በጣም ወድጄዋለው፤ በሰርቢያ
የ14 ቀናት ቆይታዬም ከሀገር ስትወጣ እዛ
የምትመለከታቸው ነገሮች አስቸጋሪና ብዙ
ቻሌንጆችንም የሚጠይቁም ስለሆኑ እነዛን
እንዴት መቋቋም እንዳለብኝም ያወቅኩበት
ሁኔታም ስላለ ያንን አይቼ መምጣቱ
እንደጥሩ ነገርም ነው የምመለከተው፡፡
ሀትሪክ፡- በሰርቢያ የሙከራ ዕድሉን
የሰጠ ክለብ ማን ነበር? ወደ እዛ ካመራክ
በኋላስ በሙከራው ጊዜ ለአንተ የፕሮፌሽናል
ተጨዋች እንዳትሆን ያስቸገሩ ሁኔታዎች
ምን ነበሩ?
ከነዓን፡- የሰርቢያ ጉዞዬ ላይ የሙከራ
እድሉን የሰጠኝ ክለብ ኤፍ ኬ ጃርኮቭ
ይባላል፤ ይህንንም እድል ያገኘሁት ቢኒያም
በሚባል ጓደኛዬ ነው፤ ወደ እነሱ ካመራው
በኋላም የውድድር ወቅት ላይ ስለነበሩ
በመጀመሪያ ዝም ብዬ እንዳልቀመጥ በሚል
ኤፍ ኬ ሎኮሞቲቭ ከሚባል ቡድን ጋር
ለሁለት ቀን ያህል ልምምድን ከሰራው
በኋላ ከጃርኮቭ ክለብ ጋር የ4 ቀናት የሙከራ
እድል ተሰጥቶኝ ብቆይም ወደ እዛ አምርቼ
ያደረኩት ሙከራ የአጭር ጊዜና በፕሪ ሲዝን
የዝግጅት ወቅት አለመሆኑ እንደዚሁም
ከዚህ የሄድኩት በጣም ዘግይቼና ስለሆነናውድድር በጀመሩበት ወቅት መሆኑ እና በዚህን
ጊዜ ደግሞ እነሱ ለጨዋታ የሚሆን ልምምድን
የሚሰሩበት ጊዜ ስለነበር በአጭር ጊዜ ውስጥ
በሁሉም ነገር መቀናጀት ስለሚያስቸግር በዚህ
መልኩ የሙከራው ዕድል ሳይሳካልኝ ለሌላ ጊዜ
ተጨማሪ የሙከራ እድል እንደሚሰጠኝ ተነግሮኝ
ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ችያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በሰርቢያ ተጨማሪው የሙከራ
ጊዜው መች ነው የሚሰጥህ?
ከነዓን፡- የሰርቢያው ክለብ ለእኔ ሌላኛውን
የሙከራ እድል የሚሰጠኝ የአንደኛው ዙር
ውድድር እንደተጠናቀቀ ነው፡፡ ያኔ በቂ የሙከራ
ጊዜን ስለማገኝ በዛ እድል ለመጠቀም ከወዲሁ
ሰፊ ዝግጅትን አደርጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ወደ ሰርቢያ በተጓዝክበትና
የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ሙከራን ባደረግክበት
ወቅት የእነሱን ተጨዋቾች ብቃት ከእኛ ሀገር
ተጨዋቾች ጋር ስታነፃፅረው ያለውን ልዩነት
እንዴት አገኘኸው?
ከነዓን፡- የሰርቢያ የአጭር ቀናት ቆይታዬ ላይ
የሙከራን ጊዜ ሳደርግ በእኛና በእነሱ ተጨዋቾች
መካከል የተመለከትኩት ነገር ቢኖር ቴክኒኩ ላይ
እኛ ጥሩ ነገር ያለን ቢሆንም ታክቲካል ዲስፕሊን
ሆኖ በመጫወቱ፣ በአካል ብቃቱ እና በፍጥነቱ
በኩል ግን ከእነሱ ጋር ልዩነት አለን፤ የእግር
ኳሱ ላይ የእነሱ ተጨዋቾች ሁሌም ጠንካራ
ሰራተኛ እንደሆኑ ተመልክቼያለውና እነዚህን
ስራዎቻቸውን ወደ እኛ ሀገር ላይ ማምጣት
ከተቻለና ከሰራንበት ቴክኒኩ ስላለን ከሀገራችን
ውስጥ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችን ማፍራት
እንችላለን፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ
ከነዓን፡- የሰርቢያው ጉዞዬ ላይ የፕሮፌሽናል
ተጨዋችነት ሕልሜን ለማሳካት የምችልበት
ዕድሉ ቢኖረኝም ወደ ሰርቢያ ዘግይቼ በመሄዴና
ቀደም ብዬም የፕሪ ሲዝን ዝግጅቱን ባለመቀላቀሌ
በሙከራ ዕድሉ የፕሮፌሽናል ተጨዋች ሳልሆን
ቀርቼያለሁ፡፡ በቀጣይ ጊዜ ሙከራው ግን
ፕሮፌሽናል የመሆን ሕልሜን አሳካለሁ፡፡
አስተያየት ይስጡ