በአቤኔዘር አበበ
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ሦስተኛ ጨዋታ አዳማ ከተማና ሸገር ከተማ 0–0 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ አዳማ ከተማ የኳስ ቁጥጥሩን በመያዝ የተሻለ ቆይታ አድርጓል። በአህመድ ሁሴን የተደረገችው ኢላማዋን የጠበቀች ሙከራና ኢዮብ ማትያስ ያደረጋት የግብ ቋሚውን መትታ የተመለሰችው ኳስ የቡድኑ ዋነኛ የግብ ዕድሎች ነበሩ። ሸገር ከተማ በአንጻሩ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ሳያደርግ አጋማሹን ሲያጠናቅቅ፣ አዳማ ከተማ በመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃዎች ጫና ፈጥሯል።ከዕረፍት መልስ የጨዋታው ፍጥነት የቀዘቀዘ ሲሆን፣ ሁለቱም ቡድኖች ግልጽ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ተስኗቸዋል። በሄኖክ አዱኛ የሚመራው የሸገር ከተማ የተከላካይ ክፍልና የአዳማ ከተማ መከላከያ ክፍል ከፍተኛ ፈተና ሳይገጥማቸው ጨዋታውን አጠናቀዋል።
አስተያየት ይስጡ