መነሻ ገጽ ሀላባ ከተማ ሪፓርት | ሀላባ ከተማ በሊጉ ታሪክ የመጀመርያ ድሉን አሳክቷል።
ሀላባ ከተማባህርዳር ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሪፓርት | ሀላባ ከተማ በሊጉ ታሪክ የመጀመርያ ድሉን አሳክቷል።

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በሜዳው ባህር ዳር ከተማን የጋበዘው ሀላባ ከተማ በዮናታን ሀይሉ ብቸኛ ጎል 1ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያ መሉ ነጥቡን አሳክቷል።

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ሀላባ ከተማ በዮናታን ሀይሉ ብቸኛ ግብ ባህር ዳር ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ በሊጉ ታሪክ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሀላባ ከተማ ኳስን በመቆጣጠርና ወደ ግብ በመድረስ የተሻለ ብቃት አሳይቷል። በ15ኛው ደቂቃም ዮናታን ሀይሉ ያደረጋት ሙከራ የግብ ቋሚውን መትታ መመለሷ ተጠቃሽ ነበር። ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ አጋማሹን ያለ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በመጨረስ 0ለ0 ተለያይቷል።ከዕረፍት መልስ ጨዋታው እንደተጀመረ በ48ኛው ደቂቃ ዮናታን ሀይሉ ያስቆጠራት ግብ ለሀላባ ከተማ የድል ሦስት ነጥቦችን አስገኝታለች። ባህር ዳር ከተማ ውጤቱን ለመቀየር ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም ።

የመጨረሻ ውጤት

ሀላባ ከተማ 1–0 ባህር ዳር ከተማ⚽️

48′ ዮናታን ሀይሉ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...