መነሻ ገጽ ቻን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ወደ ቻን ውድድር የመመለስ እድሉን አገኘች።
ቻን

ኢትዮጵያ ዳግመኛ ወደ ቻን ውድድር የመመለስ እድሉን አገኘች።

አጋራ
አጋራ

በወርሀ ጥር (ከጥር 4 – ጥር 27) በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን(በሀገር በቀል ተጫዋቾች ብቻ የሚጫወቱበት) ውድድር ከሚሳተፉት 16 ሀገሮች አላፊ የሆኑት 15 ሀገሮች የታወቁ ሲሆን ቀሪውን 1 ሀገር ለመወሰን ኢትዮጵያና ሩዋንዳ የሚጫወቱ ይሆናል። ይህንን የቻን ውድድር ለማዘጋጀት ኬንያ ጥያቄ አቅርባ እድሉን በማግኘት ውድድሩን ለማዘጋጀት ሽርጉድ ስትል መክረሟ ይታወሳል።

ሆኖም ግን ካፍ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥናት እና ክትትል ሀገሪቷ ውድድሩን ለማዘጋጀት ብቁ አደለችም በማለት የማዘጋጀት መብቷን ነጥቆ ለሞሮኮ ሰጥቷል። ሆኖም ሞሮኮ ቀድማ ለቻን ውድድር ማለፏን ያረጋገጠች በመሆኑ የቀረው 1 ቦታ ለማን ይሰጥ የሚለው ሀሳብ ብዙ ሲያከራክር ቆይቶ በሞሮኮ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ የሆነችውን ግብፅ ውድድሩ ላይ እንድትሳተፍ ጥሪ ያስተላለፈላት ቢሆንም የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን ለቻን ውድድር ብዬ የሀገር ውስጥ የሊግ ውድድሬን አላቋርጥም በማለት ውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ከዚህም የተነሳ የአፍሪካ እግርኳስ ፌደሬሽን እድሉን ለምስራቅ አፍሪካ ሰጥቷል። በዚህም ምክንያት በሱዳን ተሸንፋ የወደቀችው ኢትዮጵያ እና በዪጋንዳ ተሸንፋ የወደቀችው ሩዋንዳ በደርሶ መልስ ተጫውተው በድምር ውጤት አሸናፊ የሚሆነው ሀገር ወደ ሞሮኮ የሚጓዝ ይሆናል። የሁለቱ ሀገሮች የመጀመሪያ ጨዋታ ጥቅምት 26 አ/አ ላይ ሲካሄድ የመልሱ ጨዋታ ህዳር 3 ኪጋሊ ላይ የሚደረግ ይሆናል። ይህ ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት መጀመሩን ያገኘነው ምንጭ ያስረዳል።

ሱዳን እና ዩጋንዳ ከምስራቅ አፍሪካ
ቡርኪናፋሶ ፣ ኮትዲቯር ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ፣ ሴኔጋል ፣ ናይጄሪያ እና ካሜሩን ከምዕራብ አፍሪካ
ሞሪታኒያ ፣ ሊቢያ እና አዘጋጇ ሞሮኮ ከሰሜን አፍሪካ
ናሚቢያ አንጎላ እና ዛምቢያ ከደቡብ አፍሪካ
ኮንጎ ከመካከለኛው አፍሪካ ለ2018 ቻን ውድድር ቀድመው ያለፉ ሀገራት ናቸው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቻንኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማዜናዎች

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ በቫር ዳኝነት ይመራል

ኢትዮጵያ በመወከል በቻን ውድድር ላይ የሚገኘው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ምሽት...

ቻንኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማዜናዎች

ሁለቱ ኢትዮጵያዊን ኢንተርናሽናል ዳኞች ለቻን ውድድር ተመርጠዋል

በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የቻን ውድድር ከሐምሌ 26 እስከ...

ቻንዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

መንግስት ለፌዴሬሽኑ 15 ሚሊዮን ተጨማሪ በጀት ፈቀደ

► መንግስት ለዋሊያዎቹ የቻን አፍሪካ ዝግጅትና ውድድር ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ብር መፍቀዱ...

ቻንዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

” ማንም ተጨዋች ምንም አይነት ብቃት ቢኖረውም ከሀገር አይበልጥም” የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

"በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ ላደረጉ ተጨዋቾች ክብር ቢኖረኝም ማንም ተጨዋች ግን...