በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የቻን ውድድር ከሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 24 ድረስ ይካሄዳል።
ካፍ ውድድሩን ለመምራት የተመረጡ የ70 ዳኞችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ሁለት ኢትዮጵያዊያንንም አካቷል።
በረዳት ዳኝነት ከተመረጡት 26 ዳኞች መካከል ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት ተካተዋል።
በቫር ዳኝነት ደግሞ 12 ዳኞች ሲካተቱ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ መመረጣቸው ተገልጿል።
- ማሰታውቂያ -



