መነሻ ገጽ Uncategorized አስራት ሀይሌ እና ደደቢት አልተለያዩም[EXCLUSIVE INTERVIW]
Uncategorized

አስራት ሀይሌ እና ደደቢት አልተለያዩም[EXCLUSIVE INTERVIW]

አጋራ
አጋራ

[EXCLUSIVELY ]

አስራት ሀይሌ እና ደደቢት አልተለያዩም

ዛሬ በተለያዩ የማህበረሰብ ገፆች እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ላይ “አስራት ሀይሌ እና ደደቢት ተለያዩ” በሚል የተሰራጨው ዜና መሰረተ ቢስ መሆኑን ሁለቱም ወገኖች በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፅ በሰጡት አስተያየት ገለፁ።

ስለ ሁኔታው ከድረ-ገፃችን የተጠየቁት አንጋፋው አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ “የተወራው ወሬ ፍፁም ሀሰት ነው፤ ሚዲያው ከየት አምጥቶ እንዳወራው የማውቀው ነገር የለም። እኔና ደደቢት አልተለያየንም። እርግጥ ነው የጆሮ ህመም አጋጥሞኛል። ህመሙ ከጀመረኝ ቢቆይም ችላ ብዬው ቆይቻለሁ። ችግሩ ሲበዛብኝ ወደ ታዋቂው ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ዶ/ር ነጋ ጋር ሄጄ ብትዘገይም ደርሰህበታል። ከዚህ ትንሽ ብትቆይ ለቀዶ ጥገና ትዳረግ ነበር በማለት ጠዋትና ማታ የምወስደው ሶስት አይነት መድሀኒት እና የእረፍት ፈቃድ ሰጥተውኛል። የጆሮዬ በሽታ ያዞረኛል፣ ሚዛን ያሳጣኛል፣ ያቅለሽለሸኛል። በመሆኑም ሀኪም ባዘዘልኝ መሰረት እረፍት ላይ ነኝ። ቡድኑን ሜዳ ገብቼ ባልመራም ለአሰልጣኞቹ መመሪያ እሰጣለሁ፤ መልበሻ ክፍል ገብቼ እመክራለሁ። ደደቢቶች ክለቡ ካልፈረሰ አንለያይም ሲሉ ሞራሌን ገንብተውልኛል። ደመወዜ፣ ጥቅማ ጥቅሜ እና መኪና ሁሉ አልተቋረጠብኝም፤ ለዚህም አመሰግናቸዋለሁ” ብሏል።

dedebit.png

– የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ሚኬኤሌ አምደመስቀል በበኩላቸው “ወሬው ውሸት ነው፤ እኛ እና አስራት አንለያይም፤ እርሱ ትልቅ ስም ያለው ሰው ነው፤ ስሙ ብቻ ይበቃናል። ከጤና ችግር ጋር በተያያዘ እረፍት ላይ ቢሆንም አሁንም ቡድኑን በልምምድ ሜዳ ላይ እያሰራ ይገኛል፤ ይህንን ማረጋገጥ የሚፈልግ ሚዲያ ካለ ነገ መጥቶ ልምምድ ሜዳ ላይ መመልከት ይችላል” በማለት ከአስራት ሀይሌ ጋር ተለያዩ የሚለው የሚዲያዎች ወሬ ውሸት መሆኑን ለሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፅ ገልፀዋል።

በምስጋናው ታደሰ እና በሙሴ ግርማይ የቀረበ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...