አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከተማ ተለያዩ የፋሲል ከተማ ክለብን ለፕሪሚየር ሊግ ያበቃውና ዘንድሮም ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን ያደረገው አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደ ጊዮርጊስ ክለቡ ትናንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ 3-1 ሽንፈትን ካስተናገደ በኃሏ ከክለቡ ጋር መለያየቱን አሳውቋል፡፡ አሰልጣኝ ዘማሪያም ከክለቡ ጋር ለመለያየቱ የጤና ችግርን በምክንያትነት የጠቀሰ ሲሆን ቡድኑ በቀጣይነት በሚደረጉት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት እንዲገጥመውም ተመኝቷል፡፡ አሰልጣኙ ዘንድሮ ህመም ላይ ሆኖ ቡድኑን ያሰለጠነ ሲሆን በሁለት ቀናት ውስጥ ለዳግም ህክምና ወደ ባንኮክ እንደሚጓዝም ተነግሯል፡፡
አስተያየት ይስጡ