አርባምንጭ ከተማ ከሳምንታት በፊት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ማሰናበቱ ተከትሎ ቡድኑን ማን ይረከባል በሚል ከተለያዩ አሰልጣኞች ጋር ክለቡ ስሙ ሲያያዝ ቆይቶል፡፡ በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ የክለቡ ቦርድ ተሰብስቦ ባሳለፈው ውሳኔ አሰልጣኝ እዮብ ማለን በአሰልጣኝነት ቀጥሯል። አርባምንጭ ከተማ ከአሰልጣኙ በተጨማሪ የተለያዩ አመራር ቦታ ላይ ያሉ ፤ የቴክኒክ ኮሚቴና የደገፊ አመራርን በማንሳት በምትካቸው በአርባምንጭ ዮንቨርሲቲ በማስተማር ላይ እሚገኙ ሌክቸረሮች እና በስፖርት ሳይንስ የተካኑ ግለሰቦችን ያካተተ አዲስ ቦርድ ሲያቋቋም ክለቡን በጊዚያዊነት ይዞ የነበረው አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደሞን በማንሳት የጨንቻ ከተማዎን አሰልጣኝ ማቲዎስ በምክትልነት ሾሟል። የቀድሞው የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ እዮብ ማለ በነገው ዕለት በከፍተኛ ሊግ ክለቡ ሀዲያ ሆሳዕና ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ጨዋታ ያለው በመሆኑ እና ሁለቱ ክለቦች (ሀዲያ ሆሳዕና እና አርባምንጭ ከተማ) ባደረጉት ስምምነት መሰረት የነገውን ጨዋታ ከመራ በኋላ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ስራውን በይፋ የሚጀምር ይሆናል።
አሰልጣኝ እዮብ ማለን በስልክ አናግረን የሚከተለውን መረጃ ሰጥቶናል። “እኔ አሁን ሀዋሳ ነው ያለሁት፤ ነገ ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ላለብን ጨዋታ ልምምድ ለማሰራት እየተጓዝኩ ነው። እኔም እንደ እናንተ ከሚዲያ ነው የሰማሁት፤ ቡድኑ ችግር ውስጥ ባለበት ሰዓት እኔን መጥራቱ አስደስቶኛል፤ ነገር ግን ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ዉል ስላለኝ ነገሮችን በህጋዊ መንገድ መጨረስ አለብን። ሆኖም እኔም ከሚዲያ ስለሆነ የሰማሁት የተጨበጠ ነገር መናገር አልችልም።” በማለት ለHatricksport.com ተናግሯል።
አሰልጣኝ እዮብ ማለ ከዚህ ቀደም አርባምንጭ ከተማን ከብሔራዊ ሊግ ወደ ዋናው ፕሪሚየር ሊግ ያሳደገ አሰልጣኝ መሆኑ ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ