መነሻ ገጽ Uncategorized አህመድ ረሺድ እና ኢትዮጵያ ቡና ይለያዩ ይሆን??? ከአህመድ ረሺድ ጋር የተደረገ ቆይታ/EXCLUSIVE INTERVIEW/
Uncategorizedሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

አህመድ ረሺድ እና ኢትዮጵያ ቡና ይለያዩ ይሆን??? ከአህመድ ረሺድ ጋር የተደረገ ቆይታ/EXCLUSIVE INTERVIEW/

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በሶስት ተጫዋቾቹ ላይ በዛሬው እለት የዲሲፕሊን ቅጣት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ተከላካዩ አህመድ ረሺድ የአንድ ወር ደሞዙን ሲቀጣ በቀጣይ ጨዋታዎች እና የልምምድ ፕሮግራሞች ላይ እንዳይገኝ እገዳ ሲተላለፍበት ፡፡  አስቻለው ግርማና ዮሐንስ በዛብህ  ደግሞ በተመሳሳይ የአንድ ወር ደሞዝ ተቀጥተዋል።​

ከቅጣቱ በኃላ አህመድ ረሺድ (ሽሪላው ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገጽ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ሽሪላው  እኔ ዶርም ተኝቼ ባለሁበት ወቅት ተደውሎ አብሮ አደጌ ለኔ እንደወንድሜ የማየው በስም እንለያይ እንጂ ወንድሜ ማለት የሆነ አብሮኝ ያደገ ወንድሜ እንደሞተ ተነግሮኝ ደንግጬ ከካምፕ እራሱ እንዴት እንዴት እንደወጣሁ አላስታውስም ነበር ቀብር ላይ ሆኜ ተደውሎ ስብሰባ እንዳለ ሲነገረኝ ወንድሜ ሞቶ ቀብር ላይ ነኝ ያለሁት ስለዚህ መምጣትአልችልም አልኩኝ እነሱም እሺ አሉኝ በ ስንተኛው ጊዜ የቀራችሁበትን ምክንያት በደብዳቤ አስገቡ ተባልን  በሃዘን ምክንያት እንደቀረሁ ደብዳቤ ጽፌ አስገባሁ። ወዲያውኑ ተቀጠሃል አሉኝ እኔ እንደዚህም አልጠበኩም ነበር ስሜቴ በጣም ነው የተጎዳው እኔ ለዚህ ክለብ ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ ይሄ ነገርይፈጠራል ብዬ አስቤውም ገመቼውም አላውቅም ነበር እጅግ በጣም አዝኛለሁ ስሜቴ በጣም ጥሩ አይደለም በዚያ ላይ የኔ ቤንች እና ኦቨር ቤንች የሆኑ ተጫዋቾች እራሱ ከሚከፈላቸው እጅግ በጣም ያነሰ ክፍያ ነው የሚከፈለኝ እኔ ክለቡን ስለምወድ ብቻ ነው እጫወት የነበረው አንድም ቀን የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ አንስቼ አላውቅም የብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ነኝ በዚህ ደሞዝ የምጫወት ብቸኛው የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ነኝ ለክለቡ ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ ከታች ጀምሮ ብዙ ታሽቻለሁ ለክለቡ እና ለደጋፊዎች የተለየ ፍቅር አለኝ አመራሮቹ ላይ ያለውን ጫና አቅጣጫ ለማስቀር ይመስለኛል ኮንትራቴ ሰኔ 30 ይጠናቀቃል አሁን ባለው ሁኔታ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የምቀጥል አይመስለኝም  ሲል ለሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ገልፀዋል፡፡  

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...