በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት እና ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።
ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።
ለደደቢት ሁለቱንም ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር ለፋሲል ኤደም ኮድዞ ከመረብ አዋህዷል።
ሀዋሳ ከተማም በተመሳሳይ ወልዲያ ከተማን 2 ለ 1 የረታ ሲሆን፥ ፍሬው ሰለሞን እና ጃኮ አራፋት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ለወልዲያ ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አንዱአለም ንጉሴ ማስቆጠር ችሏል።

አርባ ምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ያለው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል።

በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተክሉ ተስፋዬ በ28ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ሳሙኤል ሳኑሚ በ48ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጓል።

የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል ጅማ ላይ ተቀዳጅቷል ዝርዝሩን ይህን ተጭነው ይመልከቱ
ደረጀ ሰንጠረዥ
| # | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ |
26 | 24 | 52 |
| 2 | ደደቢት |
27 | 16 | 48 |
| 3 | ሲዳማ ቡና |
27 | 9 | 47 |
| 4 | ኢትዮጵያ ቡና |
27 | 11 | 44 |
| 5 | አዳማ ከተማ |
27 | 8 | 44 |
| 6 | ፋሲል ከተማ |
26 | -1 | 38 |
| 7 | መከላከያ |
27 | -8 | 35 |
| 8 | ሀዋሳ ከተማ |
27 | 1 | 34 |
| 9 | 27 | -1 | 33 | |
| 10 | አርባምንጭ ከተማ |
27 | -3 | 32 |
| 11 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ |
27 | -2 | 29 |
| 12 | ወላይታ ድቻ |
26 | -10 | 29 |
| 13 | ጅማ አባቡና |
27 | -5 | 28 |
| 14 | ድሬዳዋ ከተማ |
27 | -10 | 28 |
| 15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
27 | -13 | 25 |
| 16 | አዲስ አበባ ከተማ |
26 | -16 | 19 |














አስተያየት ይስጡ