መነሻ ገጽ Uncategorized ​በድሬዳዋ ከነማ ላይ የተላለፈው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይታያል|ፌዴሬሽኑ ለሚዲያዎች በላከው E-mail…
Uncategorized

​በድሬዳዋ ከነማ ላይ የተላለፈው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይታያል|ፌዴሬሽኑ ለሚዲያዎች በላከው E-mail…

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፒሊን ኮሚቴ በድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ላይ ያሳለፈው በዝግ ስታድየም የሚካሄድ የአንድ ጨዋታና የብር 75‚000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ቅጣት  ክለቡ ባቀረበው አቤቱታ ምክንያት በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይታያል፡፡  በድሬዳዋ ስታድየም ድሬዳዋ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና የ22ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ባካሄዱበት ወቅት በተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር መነሻ ድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ በሜዳው ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች አንዱን በዝግ ስታዲየም ያለተመልካች እንዲጫወትና 75‚000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም የድሬዳዋ ከነማው የህክምና ባለሙያ አስራት ለገሠ አራት ጨዋታና 5‚000.00 /አምስት ሺህ ብር፤/ የኢትዮጵያ ቡናው ጋቶች ፖኖም ደግሞ የአንድ ጨዋታ ቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው አይዘነጋም፡፡

ይሁንና የድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ውሣኔውን በመቃወም በጠየቀው ይግባኝ መሠረት ጉዳዩ በይግባኝ ሰሚ ቋሚ ኮሚቴ ታይቶ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ በዲሲፒሊን ኮሚቴ የተላለፈው ውሳኔ በክለቡ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ በዝግ ስታድየም የሚካሄድ ጨዋታ አፈፃፀም ከውሣኔው በኋላ በሊግ ኮሚቴ የሚታይ ይሆናል፡፡
የኢትዮጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...