መነሻ ገጽ Uncategorized በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በኘሪሜየር ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ክለቦች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል
Uncategorized

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በኘሪሜየር ሊግ እና በከፍተኛ ሊግ ክለቦች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል

አጋራ
አጋራ

 

Ethiopia_FA

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ እና የይግባኝ ኮሚቴ በ2009 ዓ.ም በተሻሻለው የዲስፕሊን መመሪያ መሠረት የዳኞችና የታዛቢዎችን ሪፖርት በመመርመር የሚከተሉትን የቅጣት ውሳኔዎች አስተላልፈዋል፡፡

ሚያዝያ 07 ቀን 2009 ዓ.ም በ10፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛው ዙር እግር ኳስ ጨዋታ በተካሄደበት እለት፡-
የሁለቱም ቡድን ደጋፊዎች የየክለባቸውን ዓርማ በለበሱ ደጋፊዎች መካከል በድንጋይ እና በቁሳቁስ መወራወራቸውን አስመልክቶ ከጨዋታ አመራሮች ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በዚህ መሠረት የሁለቱም ቡድን ደጋፊዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በመሆን ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 65 በተራ ቁጥር 5 መሠረት፡-
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ብር 40‚000.00 /አርባ ሺህ ብር/፣
የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ብር 40‚000.00 /አርባ ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከዚህ ቀደም የክለቡ ደጋዎች በአዳማ ስታዲየም ከስፖርታዊ ጨዋነት የወጣ ጥፋት በመፈፀማቸው መቀጣታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ቡድኑ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ጋር በ7/08/2009 ዓ.ም ውድድር ባደረገበት ዕለት የክለቡን ዓርማ የለበሱ ደጋፊዎች የቅዱስ ጊዮጊስ ቡድን ተጨዋች የሆነውን አዳነ ግርማን ስም እየጠሩ በጽሑፍ መገለፅ የማይገባው ፀያፍና ድብ በተደጋጋሚ ስለመሳደባቸው ከውድድር አመራሮች ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲኘሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 68 በተራ ቁጥር 6 መሠረት ብር 75‚000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከአዳማ ቡድን ጋር ካደረገው ጨዋታ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በተላለፈው ውሣኔ የክለቡን ደጋፊዎች ስለስፖርታዊ ጨዋነት አስተምሮ ሪፖርት እንዲልክ የደረሰው ቢሆንም፤ በሚዲያ በኩል እያስተማረ ያለው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲኘሊን መመሪያ ክፍል 5 ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 101 በፊደል “ከ” መሠረት ደጋፊዎቹን ስለስፖርታዊ ጨዋነት እና ደንብና ሕና በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስተምረው ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት እንዲያደርጉ ተወስኗል፡፡
ሚያዝያ 05 ቀን 2009 ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት በወራቤ ስታዲየም ስልጤ ወራቤ ከሀድያ ሆሳዕና የከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር 18ኛ ሣምንት የእግር ኳስ ጨዋታቸውን ባደረጉበት ዕለት፡፡
ጨዋታው በተጀመረ በ36ኛው ደቂቃ ላይ በተለምዶ ካታንጋ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የነበሩ የሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ድንጋይ በመወርወራቸው ምክንያት ጨዋታው ለ25 ደቂቃ ተቋርጦ የቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ቴራሞ ከፖሊስ ኃይል ጋር በመሆን ባደረጉት የማረጋጋት ጥረት እና በሜዳ ውስጥ የነበሩ ድንጋዮች ተለቅመው ከወጡ በኋላ ጨዋታው እንደገና ሊቀጥል ችሏል፡፡
የዕለቱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሀድያ ሆሳዕና ቡድን ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ድንጋይ በመወርወር እና ረብሻ በመፍጠራቸው ምክንያት የፀጥታ አስተባባሪ ፖሊሶች ረብሻውን ለማስቆም ባደረጉት ጥረት በፖሊስ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ ውድድሩን የመሩትን ዳኞች ከጨዋታ ሜዳ አናስወጣም በማለታቸው እስከ ምሽቱ 12፡30 በሜዳ ላይ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡
የፀጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ባደረጉት ጥረት ረብሻውን በማስቆም ዳኞች በቀይ መስቀል መኪና ከሜዳ ወጥተው ወደ አረፉበት ሆቴል ያደረሷቸው ስለመሆኑ የጨዋታ አመራሮች በጽሑፍ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በዚህ ዓመት ሀድያ ሆሳዕና እግር ኳስ ቡድን በሜዳው እና ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ደጋፊዎቹ ከስፖርታዊ ጨዋነት ስነ-ምግባር ውጭ በመሆን ሁከትና ብጥብጥ በመፈፀማቸው ምክንያት የተለያዩ ቅጣቶች የተጣለባቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡
በእዚሁ መሠረት፡-
የሀድያ ሆሳዕና ቡድን ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ድንጋይ በመወርወር ረብሻ እንዲፈጠር፣ የአነሳሱ በመሆናቸው ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ ከሜዳቸው ውጭ እንዲጫወቱ የተለያዩ ቅጣቶች ቢቀጡም ሊማሩበት ባለመቻላቸውና ደጋፊዎቻቸው በተደጋጋሚ ለፈፀሙት ጥፋት በአካል ጉዳት ምክንያት በመሆኑ በማድረሳቸው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 በአንቀጽ 68 በተራ ቁጥር 5 መሰረት ቡድኑ ካጠራቀመው ነጥብ ላይ 6 /ስድስት/ ነጥብ እንዲቀነስባቸው ተወስኗል፡፡
በኢ.እ.ፌ ዲስፕሊን መመሪያ ክፍል 5 በምዕራፍ 3 በአንቀጽ 101 በፊደል ተራ ከ መሰረት በ30 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት እና የስፖርቱ ሕግ ስልጠና ፕሮግራም በማዘጋጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተው ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት በጽሑፍ ሪፖርት እንዲያደርጉ ተወስኗል፡፡
የሀድያ ሆሳዕና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ቴራሞ የክለቡ ቡድን መሪ ደጋፊው ከስፖርታዊ ጨዋንት ውጭ የሆነ ተግባር ሲፈፅሙ የማረጋጋት ሥራ በመስራት ላደረጉት ጥረት የዲስፕሊን ኮሚቴ በደብዳቤ ምስናግና እንዲደርሳቸው ወስኗል፡፡

የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሣኔ
በተሻሻለው የዲስኘሊን መመሪያ በምዕራፍ /በአንቀፅ 110 በንዑስ አንቀፅ 1 ሀ-ለ ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይግባኝ ባይ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ መጋቢት 8/2009 ዓ.ም ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም በተጫወቱበት ዕለት በተፈፀመው ጥፋት ለተላለፈው ውሣኔ ቅሬታቸው በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንዲታይላቸው አቅርበዋል፡፡
ድርጊቱ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋዎች ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆነ ባህሪ አሳይተዋል በማለት የብር 75‚000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ የገንዘብ ቅጣት መጣሉ አግባብ አይደለም በማለት፣
ከፍተኛ የዳኝነት በደል እንደደረሰባቸው፣
የአዳማ ከተማ ተጫዋች የሆነው ፋሲካ አስፋው የድርጊቱ መነሻ ነው ሲሉ የመከራከሪያ ነጥባቸውን /ሃሣብ/ በተጨማሪም የቪዲዮ ማስረጃ አቅርበዋል፡፡
ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴውን ክለቡ ያቀረበውን የመከራከሪያ ነጥብ እና በጨዋታው ቀን የጨዋታው አመራሮች እና የጨዋታው ታዛቢ ያቀረቡት ሪፖርት በጥልቀት በመመርመር፡-
ረዳት ዳኛ ቁጥር 1 በግራ በጥላ ፎቅ በኩል የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ውሃ በያዘ ኘላስቲክ መመታቱን፣
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ደጋፊዎች ዳኛውን ሌባ ሌባ በሚል መሳደባቸውን፣
የአዳማ ከተማ ተጨዋች ፋሲካ አስፋው በፈፀመው ጥፋት በዲስኘሊን ኮሚቴ መቀጣቱ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ጥፋት ማካካሻ ሆኖ ሊቀርብ እንደማይችል ታይቷል፡፡
የቀረበው የቪዲዮ ቪሲዲም ተጫዋች ፋሲካ በፈፀመው ጥፋት መፀፀቱን እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፈዎች የሰሩትን የጥፋት ድርጊት የሚያስተባብል ሆኖ አልተገኘም፡፡
በእዚህ መሠረት፡-
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ደጋፊዎች በዕለቱ የፈፀሙት ጥፋት ላይ በዲስኘሊን ኮሚቴ ታይቶ በተወሰነው መሠረት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ጥፋት ነው ብሎ ተቀብሎታል፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የዲስኘሊን ኮሚቴ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስኘሊን መመሪያ ክፍልን ምዕራፍ 3 በአንቀፅ 68 ተ.ቁ 5 መሠረት ብር 75‚000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ እንዲቀጣ የተወሰነው እንዲፀና ተወስኗል፡፡
ለይግባኝ ያስያዙት ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ሂሣብ ክፍል ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሚዲያዎች በላከው የኢሜል መልእክት ገልጿል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...