መነሻ ገጽ Uncategorized በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተው ወጠዋል
Uncategorized

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተው ወጠዋል

አጋራ
አጋራ

ሁለት ሳምንታትን እረፍት ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ ሲጀመር ኢትዮጵያ ንግድ

ባንክ ከወልድያ ከተማ አቻ ተለያይቷል። 9 ስዓት ላይ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው።

በዚህም ወልድያ 20 ነጥቦችን በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ14 ነጥቦች 14ኛ ደረጃን ይዟል።

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ለአራት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን፥ ሁለቱም አንድ አንድ አሸንፈዋል፤ በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል።

ንግድ ባንክ እና ወልድያ ከተማ በመጀመሪያው ዙር የሊጉ መርሃ ግብር ባደረጉት ጨዋታ ወልድያ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ ሌላው ዛሬ የተካሄደው የኢትዮ ኤሌክትሪክእና ጅማ አባ ቡና ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡

ሊጉ ነገም ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም ደደቢት ከኢትዮጵያ ቡና፣ አርባምንጭ ላይ ደግሞ አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ 9 ስአት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ጎንደር ላይ ፋሲል ከተማ 9 ስአት ላይ ሲዳማ ቡናን ሲያስተናግድ፤ አዲስ አበባ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከአዳማ ከተማ በተመሳሳይ 10 ስአት ላይ ይጫወታሉ።

መከላከያ ደግሞ 11 ስአት ከ30 ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናግዳል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ይገኛል። ደደቢት በ27፣ ፋሲል ከተማ እና አዳማ ከተማ በእኩል 26 ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ጅማ አባቡና እና አዲስ አበባ ከተማ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ይገኛሉ።

ኮከብ ግብ አግቢነቱን ደግሞ ጌታነህ ከበደ በ11 ጎሎች ሲመራ፤ ሳላዲን ሰይድ፣ ፍፁም ገብረማርያም እና አዳነ ግርማ በእኩል 7 ጎሎች ይከተሉታል።




 

ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...