መነሻ ገጽ ሪፖርት በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድሉን ሲያገኝ ፋሲል ከተማ እና ወልድያ ከተማ አቻ ተለያይተዋል።
ሪፖርትኢትዮ-ኤሌክትሪክወልዋሎወልዲያፋሲል ከተማ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድሉን ሲያገኝ ፋሲል ከተማ እና ወልድያ ከተማ አቻ ተለያይተዋል።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ አዲስ አዳጊውን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናገደው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የ3-1 አስደንጋጭ ሽንፈት ደርሶበታል። 
ለወልዋሎ አ.ዩ. ፕሪንስ ሶቨርን 16ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ በማድረግ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል። በሁለተኛው አጋማሽ በ1 ደቂቃ ልዩነት 60 እና 61ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ተሰማ እና አፈወርቅ ሀይሉ ያስቆጠሯቸው ግቦች ወልዋሎ አ.ዩ. አሸናፊ ማድረግ ችለዋል። አልሀሰን ካሉሻ 88ኛው ደቂቃ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ ግብ ማስቆጠር ቢችልም ቡድኑን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም። 


በሌላ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከተማ እና ወልድያ ከተማ ተገናኝተው ያለምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። 94ኛው ደቂቃ ላይ የወልዲያ ከተማ ተከላካዮች ኳስ በእጅ በመንካታቸው የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት አብዱራህማን ሙባረክ (ግሪዳው) ሳይጠቀምበት በመቅረቱ ፋሲል ከተማ ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ወልዋሎ ናይጄሪያዊ አጥቂ አስፈረመ

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አራተኛውን የአጋማሹን አዲስ ፈራሚ በእጃቸው አስገብተዋል። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ...

ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ወልዋሎዎች አማካዩን የግላቸው አደረጉ

ከፈረሰኞቹ ጋር የተለያየው አፈወርቅ ሐይሉ የቀድሞው ክለቡን ተቀላቀለ። በአማካይ ስፍራ ላይ ከተጠናቀቀው...