መነሻ ገጽ Uncategorized በኘሪሜየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ሲያሸንፉ ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርቷል 
Uncategorized

በኘሪሜየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ሲያሸንፉ ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርቷል 

አጋራ
አጋራ

 

በ25ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ተካሂዷል።

ከቀትር በኋላ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአዳማ ከተማ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

አዲስ ህንጻ፣ ዳዋ ሁቴሳ እና ሙጂብ ቃሲም ለአዳማ ከተማ የአሸናፊነት ጎሎችን ሲያሰቆጥሩ ለአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ አሊ አያና ማስቆጠር ችሏል።

ክልል ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ሃዋሳ ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ ደግሞ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

አስቻለው ግርማ የአሸናፊነቷን ጎል ለኢትዮጵያ ቡና ማስቆጠር ችሏል።

ጅማ ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው ጅማ አባ ቡና በበኩሉ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ለጅማ አባቡና  ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል በ91ኛ ደቂቀ ላይ ሀይረዲን ሸረፋ የማሸነፊያዋን ጎል አስቋጥሯል

FB_IMG_1493142321347-1

10 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ሊጉ ነገም ሲቀጥል ደደቢት ከድሬዳዋ ከተማ 8 ሰዓት ከ 30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ 10 ከ 30 ላይ ይካሄዳል።

ክልል ላይ በሚደረግ ጨዋታ ወልድያ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናግዳል።

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እያለው ከሲዳማ ቡና ጋር 43 ነጥብ በመያዝ በጎል ልዩነት ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ በእኩል 42 ነጥብ ይከተላሉ።

ነገ የሚጫወተው ደደቢት በ41 ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዟል።

ወላይታ ዲቻ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ አሁንም የሊጉን ግርጌ ይዘዋል።

 ደረጃ ሰንጠረዥ 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...