አሌክሳንድርያ ቡርጅ ስታድየም ላይ የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ አል እህሊ ሁለት ለ ዜሮ እሸናፊነት ተጠናቋል።
በ4-2-3-1(ኳስ በሚያጡበት ጊዜ ወደ 4-5-1 በሚቀየር) ወደ ሜዳ የወረዱት ጅማዎች በመጀመርያው 45 በሁለቱም መስመሮች በእል እህሊ ተጨዋቾች የተሰነዘረባቸው የማጥቃት እንቅስቃሴዎች መቋቋም ቸግርዋቸው ታይቷል፤በተለይ ቀኝ መስመር ላይ የተሰለፋት የመስመር ኣማካዩ እህመድ ሃሞውዲ ና ራሚ ራብያ በኩል ሚደረጉ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ግራ ተከላካይ መስመር ላይ የተሰለፈው ኤልያስ ኣታሮ መቆጣጠር ቸግሮት ታይቷል።የዚህ ማጥቃት እንቅስቃሴ ውጤትም በ7ኛው ደቂቃ ከግራ መስመር በጥሩ ቅብብል የሄደው ኳስ የቀኝ መስመር ተለላካዩ ራሚ ራብያ መትቶት ቋሚ ብረት መልሶት የመጣውን ኳስ ናሰር ማሀር እስቆጥሮት እል እህሊዎችን መሪ ማድረግ ችሏል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ጅማዎች ኳስን በመያዝ ለማጥቃት ቢሞክሩም እብዛኞቹ ኳሶች የተቆራረጡ መሆናቸው የጠራ የግብ እድል እንዳይፈጠር ምክንያት ሆነዋል።የእንድ ግብ መሪነታቸውን ከፍ ለማድረግ ማጥቃታቸውን የቀጠሉት እል ኣህሊዎች በ37ኛው ደቂቃ ላይ ግዙፋ ኣጥቂ ማርዋን ሞህሰን ከቀኝ መስመር እየተነሳ ጅማዎችን ሲያስቸግር የነበረው እህመድ ሃሞውዲ ያሾለከለትን ኳስ በሚገባ በመጠቀም የግብጹ ክለብ መሪነትን ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችሏል።የመጀመርያው 45 ማገባደጃ ላይ መሃል ሜዳ ከይሁን እንደሻው ጋር የተጣመረው ሄኖክ ገምቴሳ የእስቻለው ግርማን እንቅስቃሴ በማየት መሃል ለመሃል ያሾለከው ሰንጣቂ ኳስ እስቻለው ከተከላካዮች መሃል ሾልኮ በማለፍ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ጅማዎች በሁለተኛው እጋማሽ ከመጀመርያው በተሻለ ኳሱን ተቆጣጥረው ለመጫወት ሙከራ ቢያደርጉም አሁንም በተመሳሳይ በሜዳው መጨረሻ ክፍል(final third) ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ሲበላሽባቸው ነበር በዚህም የተነሳ ከርቀት በእወት ገ/ሚካኤል፣እስቻለው ግርማ ና በሄኖክ ገምቴሳ ከሚደረጉ ሙከራዎች ውጪ ይህ ነው ሚባል እስደንጋጭ የግብ ሙከራ ማድርግ ሳይችሉ ቀርተዋል።እል እህሊዎችም ከመጀመርያው 45 እንጻር ደከም ያለ እንቅስቃሴ ቢያሳዩም በመልሶ ማጥቃት እድሎችን ሲፈጥሩ ነበር በተለይ የጨዋታው የመጨረሻ 10 ደቂቃዎች ላይ በዋሊድ ሶሊማን፣ሚዶ ጃባር እና ማርዋን ሞህሰን በኩል የደረግዋቸው ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህም መሠረት ጨዋታው በግብፁ ሃይል ክለብ እል እህሊ ሁለት ለዜሮ እሸናፊነት ተጠናቋል፤የመልሱ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት በእዲስ አበባ ስታድየም ሚካሄድ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ