መነሻ ገጽ Uncategorized በቻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊዮፓርድስ ጋር ነገ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል
Uncategorized

በቻምፒየንስ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊዮፓርድስ ጋር ነገ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ነገ 10 ስአት ላይ ያደርጋል።

በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ኮቲዲኦር በደርሶ መልስ በመርታት ወደ ጥሎ ማለፉ የገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ የኮንጎውን ተወካይ ሊዮፓርድስ ባሳለፍነው ሳምንት በኮንጎ ዶሊሴ  ከተማ በምንተስኖት አዳነ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ፈረሰኞቹ ወደ ቀጣዩ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ምድብ ድልድል ለመግባት በአዲስ አበባ በሚደረገው ጨዋታ አቻ መውጣት በቂያቸው ነው።

በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በዶሊሴ ከተማ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ምንተስኖት አዳነ በቀይ ካርድ በመውጣቱ ምክንያት በመልሱ ጨዋታ አይሰለፍም።

ነገ በሚደረገው ጨዋታ በአቻ ውጤት አልያም በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ 550 ሺህ የአሜሪካ ዶላርየሚያገኝ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...