መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ቅዱስጊዬርጊስ ከ ፋሲል ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስዳሰሳፋሲል ከተማ

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ቅዱስጊዬርጊስ ከ ፋሲል ከተማ

አጋራ
አጋራ

የሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስአበባና በክልል ስታዲዬሞች በሚካሄዱ 5 ጨዋታዎች ሲጀምር በቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ ገፃችን ፈረሰኞቹን ከ አፄዎቹ በአዲስአበባ ስታዲዬም የሚያገናኘውን ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲዬም ከቀኑ 11:30 በብቸኝነት የሚካሄደው የቅዱስጊዬርጊስና ፋሲል ከተማ ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረት አግኝቷል፡፡ፈረሰኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ ፋሲል ከተማን በሜዳው 2ለ ምንም ካሸነፉ በሇላ በ8ጨዋታዎች 3 ነጥብ አስመዝግበው አያውቁም፡፡በዛሬው ጨዋታ ፈረሰኞቹ በሜዳቸው ፋሲል ከተማን አሸንፈው የ3 ነጥብ ጥማቸውን ያስታግሱ ይሆን ????ጥያቄው ምሽቱን ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ሁለቱም ክለቦች ነገ የሚያደርጉት ጨዋታ በበርካታ ደጋፊዎች ታጂቦ የሚደረግ ከመሆኑም ባሻገር ሜዳ ላይ ለማሸነፍ የሚደረገው ትንቅንቅ ከወዲሁ የበርካቶችን ቀልብ ስቧል፡፡በተለይም ባለሜዳዎቹ ፈረሰኞቹ የዛሬውን ጨዋታ የሚሸነፉ ከሆነ የደጋፊዎች ተቃውሞ ዳግም ሊያገረሺ ይችላል፡፡በእንግዳዎቹ ፋሲል ከተማዎችም በኩል ቢሆን ቡድኑ ወልዋሎን ቢያሸንፈም ሜዳ ላይ የነበረው እንቅስቃሴ አሳማኝ ባለመሆኑ ደጋፊዎች በዛሬው ጨዋታ ከውጤትም ባለፈ የተሻለ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ይጠብቃሉ፡፡

ባለሜዳዎቹ ቅዱስ ጊዬርጊሶች ዘንድሮ ወጥ አቋምን ማሳየት ተስኗቸው፡በተደጋጋሚ ነጥብ እየጣሉ ነው፡፡ፈረሰኞቹ ኢትዮጵያን በመወከል ሲሳተፉበት በነበረው የካፍ ቻምፒዬንስ ሊግ ወደ ምድብ ድልድል ሳይገቡ በዩጋንዳው ኬሲሲኤ ተሸንፈው መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ፈረሰኞቹ በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግም ቢሆን እንደወትሮው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን ሳይችሉ ወጣ ገባ እያሉ ከዋንጫ ፉክክሩ ብዙም ሳይርቁ በቅርብ እርቀት በሊጉ መሪ ደደቢት በ5 ነጥብ ተበልጠው አሁንም በውጤት ቀውስ ውስጥ ሁነው ለሻምፒዬንነት ጠንካራ ተፎካካሪ ናቸው፡፡

እንግዳዎቹ ፋሲል ከተማዎች ዘንድሮ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ካዘዎሯቸው ተጨዋቾች አንፃር ለዋንጫው ቅድመ ግምት ከተሰጣቸው ክለቦች አምድ የሚገኙ ቢሆንም በ16 ሳምንታት የሊግ ጉዟቸው የማይገመትና ወጥ ያልሆነ እንቅስቃሴ በማድረግ ከመሪዎቹ በቅርብ እርቀት ቢገኙም ለዋንጫ በትክክልም የሚገመት እንቅስቃሴ ግን እያሳዩ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡

ከወትሮው በሌላ ገፅታ 17 ሳምንታትን የተጓዘው ሊጋችን 10 ክለቦች በፉክክሩ ውስጥ በመሆናቸው እስካሁን ሁነኛ የዋንጫ ቡድን ነጥሮ ባይወጣም ከዚህ በሇላ የሚደረጉ ጨዋታዎች የፍፃሜ ያህል ዋጋ አላቸው ፡፡በተለይም በዛሬው ጨዋታ የሚያሸንፍ ክለብ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከማስመዝገቡም ባሻገር ለቀጣዩ ጨዋታ ትልቅ የሞራል ዋጋ ይኖረዋል፡፡በዛሬው የቅዱስጊዬርጊስና ፋሲል ከተማ ጨዋታ በዋንጫ ፉክክሩ ብዙ ርቀት ለመጓዝ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል፡፡

ባለሜዳዎቹ ፈረሰኞቹ በሊግ ጨዋታ ለ6 ሳምንታት ያለድል ሲጓዙ ከሜዳቸው ውጭ በሀዋሳ ከተማ ከደረሰባቸው የ4ለ1 ሽንፈት ማግስት በ16ኛው ሳምንት ወደ ድሬድዋ አቅንተው
ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ነጥብ ተጋርተው ሲመለሱ እንግዳዎቹ ፋሲል ከተማዎች በሜዳቸው አርባምንጭ ከተማን አሸንፈው በ16 ኛው ሳምንት እዚሁ አዲስ አበባ ስታዲዬም ወልዋሎ አ/ዩን 1ለምንም አሸንፈው ሁለቱ ክለቦች የሚገናኙ ሲሆን ከፍተኛ ፉክክር የሚስተናገድበት የመዲናዋ የነገ ብቸኛ ጨዋታ ነው፡፡

ሜዳላይ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እንደገቡ የሚነገርላቸው ቅዱስ ጊዬርጊስና ፋሲል ከተማ የቡድናቸው የዘንድሮው አጨዋወት ይህነው የሚባል አይደለም፡፡ፋሲል ከተማ ከሚታወቅበት አስፈሪ የመከላከል እና የማጥቃት ቅርፁ ወጥቶ ግቦችን የሚያስተናግድ ቡድን እየሆነ ሲመጣ ፈረሰኞቹም በተመሳሳይ በአዲሱ አሰልጣኝ እየተመሩ ሜዳ ላይ በየሳምንቱ ቅርፁን የሚለዋውጥ ቡድን እየተመለከትን ነው፡፡

በፈረሰኞቹ በኩል በዛሬው ጨዋታ ሳላዲን ሰይድና ናትናኤል ዘለቀ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን የኦዶንካራ፡ አስቻለው፡አበባው መግባትም አጠራጣሪ ሁኗል፡፡በአፄዎቹ ቤት አይናለም ሀይለ አሁንም ከጉዳት ባለመመለሱ በጨዋታው የማይሰለፍ ሲሆን የፊት መስመር ተሰላፊው ራምኬል ከቅጣት መልስ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል፡፡

የእርስበርስግንኙነት

4 ጊዜ ሲገናኙ ፡ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ጊዜ ሲያሸንፍ፡ ፋሲል ከተማ 1አሸንፎ ፡በ1 ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰር ሊደረግ ነው

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀድሞው አጋሩ ጋር በድጋሚ ለመጣመር ውይይት አድርጓል። አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስን...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞው ተጫዋቾች ማህበር አቋቋሙ

የቅዱስ ጊዮርጊስን ችግር ለመቅረፍ ያለመ በቀድሞው ተጫዋቾች የተሰየመ ማህበር በዛሬው ዕለት በይፋ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሽግግር ኮሚቴ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ መረጠ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ካጋጠመው ውስጣዊ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቋቋመው የሽግግር ኮሚቴ...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፈረሰኞቹ የሰላም ውይይት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል…..

... ከሳሹ ወገን ዛሬ ቦርዱ ሃላፊነቱን መልቀቁን በይፋ ማሳወቅ አለበት እያለ ነው...