በአዲሱ መብራህቱ እና የሻነው ግዛቸ
በ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ዛሬ በክልል ስታዲዬሞች ከሚካሄዱ ጨዋታዎች አንዱ በትግራ ደርቢ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከ መቆለ ከተማ በ9:00 በአዲግራት ስታዲዬም የሚያገናኝ ጨዋታ ነው፡፡ለሊጉ እንግዳ የሆኑት ሁለቱ የትግራይ ክለቦች አጀማመራቸው ሁለቱም መልካም የሚባል ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ሊጉን በመምራት ክስተት የነበሩት ቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎዎች አሁን በወራጂ ቀጠናው አፋፍ ላይ ሁነው በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኘውን መቆለ ከተማ በደርቢ ጨዋታ ዛሬ በሜዳቸው ይፋለማሉ፡፡
ዛሬ በክልል ከሚካሄዱ 4 ጨዋታዎች ከፍተኛ ፍክክር እንደሚስተናገድበት የሚጠበቀው የትግራይ ደርቢ ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ባለፈው ሳምንት በራሳቸው መረብ ላይ ባስቆጠሩት ግብ በአዲስ አበባ ስታዲዬም በፋሲል ከተማ ሽንፈት አስተናግደው ለጨዋታው ሲቀርቡ መቐለ ከተማዎች በሜዳቸው በአርባምንጭ ከተማ ላይ 4 ግቦችን አዝንበው በማሸነፍ በትልቅ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ለጨዋታው ቀርበዋል፡፡
የጨዋታውን ውጤት ለእንግዳዎቹ መቐለ ከተማዎች ለሻምፒዮንነት በሚደረገው ፉክክር ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን አጠብቅው የሚፈልጉት ሲሆን ሊጉን እስከ መምራት የሚያደርሳቸውን አጋጣሚ የሚፈጥር ነው፡ ፡ለባለሜዳዎቹ ወልዋሎዎች ከመውረድ ስጋት ለመዳን ውጤቱ እጅጉን ያስፈልጋቸዋል፡፡በተለይም በዛሬው የሊግ ጨዋታዎች በጀረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኙት ድሬድዋ ከተማና ኢትዬ ኢለክትሪክ አሸንፈው ወልዋሎዎች ውጤት የማይቀናቸው ከሆነ ወራጂ ቀጠናውን የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የዛሬው የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ከተማ ጨዋታ ሜዳ ላይ ለማሸነፍ የሚደረገው ፍልሚያ ለተመልካች ማራኪ እንደሚሆን ከወዲሁ የሚጠበቅ ነው፡፡በመጀመሪያው ዙር በመከላከል ጠንካራ የነበሩት መቐለዎች የግብ ዕድል የመፍጠርና ያገኙትን አጋጣሚ የመጠቀም ክፍተታቸውን አሻሽለው 4 ግቦችን በተጋጣሚያቸው መረብ ላይ ከማሳረፋቸውም ባለፈ በግራ መስመር አመዝነው የግብ ዕድል ለመፍጠር ይጫዎቱ የነበረ ቢሆንም ቡድኑ ከአርባምንጭ ጋር በነበረው ጨዋታ ከየትኛውም ቦታ የግብ ዕድል መፍጠር መቻሉ ለባለሜዳዎቹ በዛሬው ጨዋታ ፈተና እንደሚሆን የሚጠበቅ ነው፡፡
ባለሜዳዎቹ ኳስን መስርተው በሁለቱ ግራና ቀኝ መስመሮች የግብ ዕድል ለመፍጠር የሚጫዎቱት ወልዋሎዎች በዛሬው ጨዋታ ይህንኑ አጨዋወት ሜዳ ላይ የሚተገብሩ ከሆነ ውጤታማ ይሆናሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡በቡድኑ በተመሳሳይ መንገድ የግብ ዕድል ለመፍጠር የሚጫዎት ከሆነ በተጋጣሚው መቐለ ከተማ በቀላሉ ሊቆም ይችላል፡፡
በጉዳትና ቅጣት ዜና የባለሜዳዎቹ ወልዋሎዎች በኩል ግብ ጠባቂው በረከት አማረ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በመጠራቱ በነገው ጨዋታ የማይኖር ሲሆን፡በእንግዳዎቹ ቤት የ3 ተጨዋቾችን፡የሀብታሙ ተከስተ፡ አሌክስ አሙዙና ጋቶች ፓኖምን ግልጋሎት አያገኙም፡፡
የእርስበርስ ግንኙነት
ሁለቱ ክለቦች በርካታ ደጋፊዎች በታደሙበት ትግራይ ስታዲዬም ለመጀመሪያ ጊዜ በኘሪሚዬር ሊግ ጨዋታ በመጀመሪያው ዙር ሁለተኛ ሳምንት የተገናኙ ሲሆን ያለግብ አቻ ተለያይተዋ፡፡
ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ይርጋለም ወልደጊዮርጊስ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል፡፡