መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | የያሬድ ዳዊት ብቸኛ ግብ ለጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ አስገኝታለች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማወላይታ ድቻየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የያሬድ ዳዊት ብቸኛ ግብ ለጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ አስገኝታለች

አጋራ
አጋራ

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በፋሲል ተካልኝ የሚመራውን አዳማ ከተማን በፀጋዬ ኪዳነማርያም ከሚመራው ወላይታ ድቻ ያገናኘ ነበር ። ሁለቱም ቡድኖች በመጀመሪያ የሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ያሳዩት ጠንካራ ሊባል የሚችል የሜዳ ላይ አቋም ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎት ነበር ።

በጨዋታው ቋሚ አሰላለፍ አዳማ ከተማ በሁለተኛው ሳምንት ጅማ አባጅፋር ከገጠመው ቡድን አንድ ቅያሪ ብቻ ያደረጉ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ግን ሀዋሳ ከተማ ያሸነፈውን ቡድንን ሙሉ ለሙሉ ይዘው ወደ ሜዳ ገብተዋል ።

ጨዋታው ፈጣን ጅማሮ የነበረው ሲሆን በተለይም በአዳማ ከተማ በኩል ኳሱን በመቆጣጠር እና ብልጫ በመውሰድ ለመጫወት የሞከሩ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ ቀጥተኛ እና ፈጣን ኳሶች ከፊት መስመር ለሚገኙት ተጨዋቾች በመላክ በተጋጣሚ ላይ ጫና ለመፍጠር ሞክረዋል ። ነገር ግን በጨዋታው 4ኛ ደቂቃ ላይ አሜ መሀመድ በሳጥን ውስጥ አግኝቶ ከሞከረው እና ኢላማውን ከሳተው ኳስ ውጪ በግብ ሙከራዎች የታጀበ አጋማሽ አልነበረም ።

የጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ የግብ ሙከራዎችን እና ከጨዋታው ሶስት ነጥብን ይዞ ለመውጣት በሁለቱም ቡድኖች በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል ። ከእረፍት መልስ 48ኛው ደቂቃ ላይ የአዳማ ከተማው አምበል ዳዋ ሆቴሳ ከርቀት አክርሮ ወደ ግብ የመታው ኳስ ለጥቂት ወቶበታል ። ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ ወላይታ ድቻዎች ከቅጣት ምት በተነሳ ኳስ በበረከት ወልደዮሐንስ አማካኝነት ያደረጉት ሙከራ በግብ ጠባቂው ተይዟል ። በ65ኛው ደቂቃ ላይ ባሳለፍነው የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ በቅጣት ምት ግሩም ግብ አስቆጥጥ የነበረው ዳዋ ጥሩ የሚባል የቅጣት ምት ወደ ግብ ቢመታም ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ ሊመልሰው ችሏል ።

በአጋማሹ አዳማ ከተማዎች በተሻለ ጫና ፈጥረው መጫወት የቻሉ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ በተፈጠረባቸው ጫና ወደ ኋላ በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማግኘት ሞክረዋል ። በጨዋታው 68ኛ ድቂቃ ላይ የጨዋታው የመጀመሪያ እና ብቸኛ ግብ ተቆጠረ ።

ያሬድ ዳዊት ከርቀት በቅጣት ምት የመታው ኳስ የአዳማ ተከላካዮችን መሀል ለመሀል አልፋ ግብ ሆነች ። ከግቧ በኋላ ባሉት ደቂቃዎች የአዳማ ከተማ ጫና እንዲሁም የወላይታ ድቻ ተጨዋቾች ጠንካራ የመከላከል ስራን ያስመለከተ ነበር ። በአዳማ ከተማ በኩል የነበረው ከባድ የማጥቃት እንቅስቃሴም አልፎ አልፎ ኳሶችን በሚቀሙ ጊዜ ለመልሶ ማጥቃት አጋልጧቸው ነበር ።

ጨዋታውም ሌላ ተጨማሪ ግብ ሳያስተናግድ በያሬድ ዳዊት ብቸኛ ግብ ወላይታ ድቻ ከሶሰት ጨዋታዎች ሁለተኛ ድሉን እንዲያስመዘግብ አስችሎታል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...

አዳማ ከተማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮጵያ ቡናና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋሩ!

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ...