በ 2016 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈዉ አዲሱ አዳጊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በክረምቱ የዝዉዉር መስኮት የነቃ እንቅስቃሴ እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል ግምባር ቀደሙ ሆኗል።
ከቀናት በፊት ኪቲካ ጅማን ከኢትዮጵያ መድህን ማስፈረም ቻለዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን ደግሞ በዚህ የዉድድር አመት በድሬደዋ ጥሩ ግልጋሎት የሰጠዉን እና በተጠናቀቀዉ የዉድድር አመት ለድሬደዋ 14 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈዉ ቢኒያም ጌታቸዉን በሁለት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸዉን ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአብዱልከሪምን ዉል ማደሳቸዉን አረጋግጠዋል።