መነሻ ገጽ Uncategorized የጨዋታ ሪፖርት|ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል ጅማ ላይ ተቀዳጅቷል 
Uncategorized

የጨዋታ ሪፖርት|ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል ጅማ ላይ ተቀዳጅቷል 

አጋራ
አጋራ

 

በ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ መርሀ ግብር ቀጥሎ ሲደረግ በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ከሜማሎ ሰንዳውንስ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታ ኘሪቶሪያ ላይ እሚያደርገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ ላይ በሰልሀዲን ሰኢድ ብቸኛ ጎል አሸንፏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን በ4-3-3 ቅርፅ አሰለፉን ሲጀምር በአንፃሩ ጅማ አባቡና በ4-5-1 ቅርፅ ወደ ሜዳ ሲገቡ ጨዋታው በተጀመረ  በ13ኛ ደቂቃ አሜ መሀመድ በግራ መስመር ብቻውን የተቆጣጠረው ኳስ ከጨዋታ ውጭ አቋቋም ላይ ነህ በሚል የመስመር ዳኛው ሲያስቆሙት ብዙም ሳይቆይ በ13ኛ ደቂቃ ላይ ከደጉ ደበበ ጎን ለጎን ሮጦ ያገኛትን ኳስ ለጥቂት ሮበርቶ ኦዶንካራ ሲያዳነበት ፡፡ በ21ኛ ደቂቃ ላይ 27ቁጥሩ ነተንቢ ክርዚስቶም ከመሀል ሜዳ መሬት ለመሬት የመታት ኳስ የጎሉን ጠርዝ ታካ ወጣለች፡፡በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በ22ኛ ደቂቃ ላይ ሰላዲን በርጌቾ ከመሀል መዳ የዟት የሄደውን ኳስ ወደ ጎል ሞክሮት ጀማል ጣሰው ሲተፋበት ጎል ስር የነበረው ሰላዲን ሰይድ በድጋሜ ሞክሮ ጀማል ጣሰው በአስደናቂ  ሁኔታ ከጎልነት አድኖታል፡፡ በጨዋታው  በ31ኛ ደቂቃ  አዳነ ግርማ መሀል ሜዳ ላይ አክርሮ የመታው ኳስ ጀማል ጣሰው በሚገርም ሆኔታ ያዳነበት እሚጠቀስ ነው፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱ ክለቦች በኩል እሚጠቀሱ ሙከራዎች ነበሩ፡፡


በሁለተኛው አጋማሽ በ52ኛ ደቂቃ ላይ ተስፋዬ አለባቸው ከ ጀማል ጣሰው ጋር በፈጠሩት መጎሳሰም የመሀል ደኛው ተስፋዬ አለባቸውን በቀይ ካርድ ከሜዳ አሰናብተዋል፡፡

በ54ኛ ደቂቃ ላይ ሳላሃዲን ሰኢድ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባር በመግጨት ከመረብ አሰርፎ ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ ሲያደርግ ለራሱ በሊጉ 15ኛ ጎሉን አስቆጥሯል ፡፡
ከጎል መቆጠረ በኅላ ጅማ አባ ቡና ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ሲወረውሩ ተያይቷል፡፡

በጨዋታው በ70ኛ እና በ73ኛ ደቂቃ ላይ  ዳዊት ተፈራ አክርሮ የመታት ኳስ በጎሉ አናት  ሲስዳት ብዙም ሳይቀይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ጎል ክልል ውስጥ አስቻለው ያአስቀረበት እሚጠቀስ ነው፡፡ ከሁለተኛው አጋማሽ በኃላ ከባድ ዝናብ ሲጥል በሁለቱም ክለቦች የተጫዋቹ ቅያሪ ሲደረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በ74ኛ ደቂቃ ፕሪንስ ወጥቶ ራምኬሎ ሎክ ;እዲሁም በ 88ኛ ደቂቃ ላይ አዳነ  ወጥቶ አብደልከሪም ገብተዋል፡፡በጅማ አባቡና በኩል  ነተንቢ ወጥቶ ቢንያም እንዲሁም ሄኖክ ወጥቶ ቴድሮስ አስገብተዋል፡፡

ጨዋታው ሊጠናቀቅ 5ደቂቃ ሲጨመር በ91ኛ ደቂቃ ላይ ጅማ አባቡናዎች የመአዘን ኳስ  አጊንተው ሳይጠቀሙበት ቀርተው ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ከጨዋታው መጠናቀቀ በኃላ በስታዲየሙ በደጋፊዎቻቸው መከላከል  ስርአት አልበኝነት ተይቷል፡፡

pic-credit የፈረሰኞቹ ገጽ

ደረጃ ሰንጠረዥ 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...