መነሻ ገጽ Uncategorized ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ተረከበ 
Uncategorized

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ተረከበ 

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ በሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም የቡና ደርቢን አስተናግዷል።

Buna

በጨዋታው ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ መረከብ ችሏል።

ሲዳማ ቡናዎች በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ባስቆጠሩት ጎል መምራት ሲችሉ፥ ኢትዮጵያ ቡናዎች ደግሞ ለእረፍት ሲቃረቡ ባስቆጠሩት ጎል አቻ መሆን ችለው ነበር።

ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡናዎች ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ጨዋታውን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል።

በዚህም ሲዳማ ቡና የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት በ36 ነጥቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረክቧል።

በአንጻሩ ኢትዮጵያ ቡና በመሸነፉ ምክንያት ባለበት 32 ነጥብ ላይ የሚቆይ ይሆናል።

የዛሬው ጨዋታ በተለያዩ ድርጅቶች ስፖንሰር በመደረጉና ገቢው ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚውል በመሆኑ፥ በርካታ ተመልካቾችን ለማሳተፍ ጨዋታው በሃዋሳ ስታዲየም እንዲደረግ ተወስኗል።

ሊጉን ሲዳማ በ36 ነጥቦች ሲመራ አንድ ጨዋታ የሚቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት እኩል 35 ነጥብ በመያዝ ይከተላሉ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ በ15 ግርጌውን ይዘዋል::

የደረጃ ሰንጠረዥ  እና ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ይመልከቱ



 

 



ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...