በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በግምት ከ60 ሺህ በላይ ደጋፊ የታደመበት ትግራይ ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መሪዎቹ መቐለ 70 እንደርታ ደደቢት ላይ ድል ካስመዘገበው ቡድን ስዩም ተስፋዬን በቢያድግልኝ ኤልያስ፣ፊሊፕ ኦቮኖን በሶፈንያስ ሰይፈ ሲቀይሩ፤ ወልዋሎ በበኩላቸው ሃዋሳን ካሸነፈው ቡድን ራችሞንድ ኦዶንጎን በክርስቶፈር ችዞባ እንዲሁም በ እምስት ቢጫ ምክንያት ያልተሰለፈው ብርሀኑ ቦጋለ ምትክ እንየው ካሳሁን ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል።

ከኃላ ሥስት ተከላካዮችን በመጠቀም በ 3-4-1-2 ኣሰላለፍ ወደ ሜዳ የወረዱት ወልዋሎ የመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ላይ የጨዋታ ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።በሁለቱም መስመር የተሰለፋት ኤፍሬም አሻሞ እና እንየው ካሳሁን ሜዳውን ወደ ጎን በመለጠጥ ከመስመር በሚነሱ ኳሶች በፕሪንስ ሰርቪንሆ እና አብዱራህማን ፋሴይኒ እማካኝነት የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችለዋል።መቐለዎች በበኩላቸው በ4-4-2 (ዳይመንድ ቅርጽ) ኣጨዋወት በእጭር ቅብብልና ፊት ኣጥቂዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ረጃጅም ኳሶችን በኩል ለማጥቃት ያደረጉት ሙከራ በቀላሉ በወልዋሎ ተከላካይና ኣማካይ ክፍል ተጨዋች ሲጨናገፍባቸው ታይቷል።በመቐለ የመጫወቻ ሜዳ ላይ በቁጥር በዝተው ጫና ሲፈጥሩ የነበሩት ወልዋሎዎች የጫናቸው ውጤት ጨዋታው በተጀመረ በ19ኛው ደቂቃ ከግራ መስመር ፕሪንስ ሰርቪንሆ ከእሌክስ ተሰማ የነጠቀውን ኳስ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን አሻግሮት እንየው ካሳሁን በድንቅ አጨራረስ ቢጫ ለባሾቹን መሪ አድርጓል።ከግቡ መቆጠር በኃላ መነቃቃት ያሳዩት መቐለዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው ቢታዩም የሜዳው የመጨረሻ ክፍል(final third) ላይ የነበራቸው ያለ መናበብ ከቆሙ ኳሶች ከሚፈጥርዋቸው እድሎች ውጪ የጠራ የግብ እድሎችን እንዳይፈጥሩ እድርጓቸዋል።የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው መጫወታቸውን የቀጠሉት ምዓም እናብሶች በ30ኛው ደቂቃ ላይ ኦሰይ ማውሊ በወልዋሎ ግራ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ መሬት ለመሬት አሻምቶት ያሬድ ከበደ በጥሩ አጨራረስ መቐለን አቻ ማድረግ ችልዋል።

ሁለተኛው እጋማሽ በመቐለ 70 እንደርታዎቹ ብልጫ ሲጀምር ወልዋሎዎች ወደ ኃላ እፈግፍግው መልሶ ማጥቃትን ምርጫቸውን እድርገዋል።መሃል ሜዳውን በማጥበብ ለሁለቱም የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ ያሬድ ሃሰን እና ቢያድግልኝ ኤልያስ በማጥቃቱ ላይ እንዲሳተፋ ክፍተት ሚፈጥረው የመቐለ አጨዋወት ስልት በዛሬው ጨዋታ ውጤታማ መሆን ሳይችል ቀርቷል።የዚህ ማሳያ ሚሆኑት መሃል ላይ በጥሩ ቅብብል ወደ መስመር ሚወጡት ኳሶች በቀላሉ ሲበላሹ ታይቷል።ተደጋጋሚ ጥፋቶችና መቆራረጥ የታየበት ሁለተኛው እጋማሽ ኣልፎ አልፎ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ሙከራዎችን ታይተውበታል።መቐለዎች በኦሰይ ማውሊ በኩል ያደረጉዋቸው ሙከራዎች በበረከት እማረ እና በግቡ አግዳሚው ሲመለሱ፣የዮውሃንስ ሳህሌ ቡድን ወልዋሎም እብዱራህማን ፋሴይኒን ቀይሮ በገባው ራችሞንድ አዶንግ እማካኝነት ያደረጓዋቸው ሙከራዎች ሶፈንያስ ሰይፈ አምክንዋቸዋል።

በዚህም መሰረት ታላቁ ትግራይ ደርቢ በመጀመርያ እጋማሽ በተቆጠሩ ግቦች በአቻ ውጤት ተጠናቋል፤በውጤቱም መሰረት የፕሪምየር ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ነጥቡን 39 ሲያደርስ ወልዋሎ ዩኒቨርሲቲ ዓዲግራቶች ነጥባቸውን ወደ 24 ከፍ ማድረግ ችለዋል።
በጨዋታው ላይ የተቆጠሩ ግቦችን በቪዲዮ ይመልከቱ
አስተያየት ይስጡ