
ዛሬ በተካሄደው የካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የማዳጋስካሩ አህመድ አህመድ የኢሣ ሃያቱን የ 29 ዓመት አገዛዝ 34 ለ 20 በሆነ ድምፅ በማሸነፍ የኢሣ ሃያቱ ሥርወ መንግሥት መገርሰሱ ይታወሳል።

አሁን ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ለካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ፍክክር ኢትዮጵያ አቶ ጁነዲን ባሻህ በመጨረሻው ሠዓት ራሳቸውን ከፉክክሩ ዉጪ(ሪዛይን)በማድረጋቸው ኢትዮጵያ በካፍ የመወከል ዕድሉን ስታጣ ጅቡቲ 1ኛ በመዉጣትዋ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዉስጥ መግባት ችላለች።መጀመሪያ በተደረገው ምርጫ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት በ20 ድምፅ 1ኛ የሱዳኑ ዋና ፀሐፊ በ12 ድምፅ 2ኛ አቶ ጁነዲን ባሻህ በ9ድምፅ 3ኛ የኡጋንዳው በ7ድምፅ መጨረሻ በመውጣታቸውና ከ50 በላይ የሚለውን የምርጫ ህግ ባለማማላቱ ምርጫው እንዲደገም በመወሰኑ 3ኛ የወጡት አቶ ጁነዲን በድጋሚ ቢወዳደሩም መውደቃቸው አይቀሬ መሆኑን በማመን ራሳቸውን ከፉክክሩ በማውጣት ሪዛይን በማድረግ ድምፃቸውን ለጅቡቲው ተወዳዳሪ ሙሉ በሙሉ በመስጠታቸው ማለትም መጀመሪያ ያገኙትን 9 ነጥብ ለጅቡቲ ለመስጠት በመወሰናቸው መጀመሪያ በ20 ድምፅ 1ኛ የነበሩት የጅቡቲው ዕጩ በ29 አጠቃላይ ድምፅ 1ኛ በመሆን የካፍ ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ሲገቡ 12 ድምፅ ያገኙት የሱዳኑ ዕጩ በ2ተኛነት አጠናቀዋል ።
አስተያየት ይስጡ