ሀትሪክ ኤዲቶሪያል | አቶ መኮንን ኩሩ ለሀትሪክ ቃለ ምልልስ በሰጡበት ወቅት ከኃላፊነታቸው አልተነሱም

ባለፈው ሳምንት በሀትሪክ ጋዜጣ The Big Interview አምዳችን ላይ በወቅቱ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር ከነበሩት አቶ መኮንን ኩሩ ጋር ወቅታዊና አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ አድርገን እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ አቶ መኮንን ኩሩ ከኃላፊነታቸው እንዳልተነሱና የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር እሳቸው ብቻ እንደሆኑ መግለፃቸውም ይታወቃል፡፡ ይህ ቃለ ምልልስ ለንባብ ከበቃ በኋላ አቶ መኮንን ኩሩ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ ብዥታን መፍጠሩና አቶ መኮንን የተከበሩ አንባቢዎቻችንና የሀትሪክ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልን እንደዋሹ የተረዱ በርካቶች መሆናቸውን ከደረሱን አስተያየቶች ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ከአቶ መኮንን ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስ እራሳቸውን ከኃላፊነት ከማንሳታቸው በፊት መሆኑን እየገለፅን እሳቸውም ይሄንኑ አስረግጠው በመናገራቸው የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን በዚህ መልኩ እንድትረዱልን በአክብሮት እየጠየቅን፤ ላሳያችሁን ተቆርቋሪነትና እውነቱን ለማወቅ ላደረጋችሁት ጥረት ያለን አክብሮት ላቅ ያለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሀትሪክ ጋዜጣ ኤዲቶሪያል ቦርድ


ባለፈው ሳምንት በሀትሪክ ጋዜጣ The Big Interview አምዳችን ላይ የቀረቡትን የቴክኒክ ዳይሬክተር ከነበሩት አቶ መኮንን ኩሩ ጋር የነበረንን ቆይታ ከታች ባስቀመጥነው ሊንክ ያገኙታል

የአቶ መኮንን ኩሩ ዝምታን የሠበረ አነጋጋሪ ቃለ-ምልልስ “ውጪ ተምረን መጥተናል፣ ኢንተርናሽናል ላይሰንስ አለን የሚሉ ሰዎች ነገሮች ሁሉ ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዳይሆንባቸው እሰጋለሁ”

 

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team