ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለችቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ  ሃላፊነቱን ከተረከቡ ድፍን አንድ  አመት  ሞልቷቸዋል። በሀገር ውስጥ ዘገባችን  በደርሶ መልስ ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ ተሸንፈው ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውጪ የሆኑት የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ እንግዳችን  ነው…. አሰልጣኙ ከይስሃቅ በላይ ጋር  የነበራቸው ቆይታ  ክፍል አንድ ባለፈው ሳምንት በወጣችው ሀትሪክ ላይ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል የመጨረሻውና ክፍል ሁለቱ ነገ ለንባብ በምትበቃው ሀትሪክ ላይ ይጠብቁ…. አሰልጣኙ ከዳዊት እስጢፋኖስ አለመመረጥ ጋር ተያይዞ እንደተናገሩት “ከዳዊት ጋር የተለየ ችግር የለብኝም ለምን አልተመረጥኩም ብሎ መጠየቅ ሲቻል በሚዲያ ሆድ መባባሱና ጥቅስ መጥቀሱ ለምን እንዳስፈለገ አሁንም አልገባኝም”ሲሉ መልስ ሰጥተዋል። ጨምረውም” ሃሳብ ያለው የሌለው በኮታ ምናምን እያልን ህዝቡን ብዥታ ውስጥ ባንከተው ጥሩ ነው” ሲሉ በተከታታይ ለተነሳባቸው ቅሬታ ምላሽ ሰጥተዋል።

*…. የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሰኞ ይጀመራል…
*..የተጨዋቾች ደመወዝ አለመከፈሉ
*…የሀድያ ሆሳዕና ዕገዳ የትድረስ ይሆን..?
*..አዲሱ ሻምፒዮን ማን ይሆን..?
ለሚሉና ሌሎች የሊጉ እውነቶች የሚገልጽ ዘገባን ይዘናል…

*…ሲዳማ ቡናው ፍሬው ሰለሞን
/ጣቁሩ/ ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ “ለሲዳማ ቡና ምርጥ ብቃቴን አሳይቼ ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥና ፕሮፌሽናል ለመሆን እጥራለሁ”ሲል ተናግሯል….

*. …ዘንድሮ ሌላ አናስብም..ከአንድ አንድ ዋንጫ ማንሳትን አልመናል” ሲል የኢትዮጵያ ቡናው ዊሊያም ሰለሞን ከመሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል….

*… ከመሸሻ ወልዴ ጋር ቆይታ ያደረገው የሰበታ ከተማው በሃይሉ ግርማ “ከጊዮርጊስ ጋር ከምናደርገው ጨዋታ ጀምሮ በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ምርጥ የተባለ ውጤት እናስመዘግባለን” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…


በውጪው ዘገባዎቻችን ደግሞ…


*….የማን.ዩናይትዱ ዲያጎ ዳሎት ኮከቡን ክርስቲያኖ ሮናልዶ አወድሶ አይጨርስም…..”ከሮናልዶ ጎን መጫወት ትልቅ ዕድል ነው” ሲል አወድሶታል።

*…ማን.ዩናይትድ በመሃል ተከላካዮች ጉዳት ቀውስ ውስጥ ገብቷል…በዚህ ዙሪያ ዘገባ ይዘናል…

*…. የመድፈኞቹ ድንቅ የመከላከል ምስጢር ተብሎ ስለተወደሰው ጋብርኤል ማጋሃሊስ የምንላችሁ ነገርም አለ…

*… የቀድሞ የሊቨርፑል ኮከብ ጂኒ ዋይናልደም ” ፒ ኤስ ጂን በመቀላቀሌ አልጸጸትም” ሲል በፓሪሱ ክለብ ቆይታ እየተደሰተ መሆኑን ገልጿል።

*…የሊቨርፑሉ ኮስታስ ሲሚካስ “ከሊቨርፑል ጋር ታላላቅ ዋንጫዎችን ማንሳት እፈልጋለሁ” ሲል ህልሙን ተናግሯል…

*…ክሊያን ምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ ማቅናት ቢፈልግም የሳንቲያጎ በርናባው በር ተከፍቶ ዝግጁ ቢሆንለትም እስካሁን ያሰበው አልተሳካም …መቋጫ ስላልተገኘለት የፒ ኤስ ጂ ቆይታው የተዘጋጀ መረጃ ይዘናል…


……እናም ሌሎች መረጃዎች….


እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት  አዳዲስ መረጃዎችን   የሚያገኙበት  ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
        የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team