ሀትሪክ ስፖርት ከእናንተ ጋር፤ ማክሰኞ ጠብቋት!
ባለቀለሟ፣ ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ለንባብ ስትበቃ የሚወዷቸውን የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ውድ አንባቢያን ለማስኮምኮም የመጨረሻው ጫፍ ላይ ደርሳ ስራዋን አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
ከሀገር ውስጥ፡- THE BIG INTERVIEW በሚለው አምዷ የኢትዮጵያ ቡናው ዳንኤል ደምሴ ለክለቡ ፊርማውን ካኖረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ባለው ቆይታ ለጋዜጣው የሰጠው ቃለ-ምልልስ አለ፤ ዳንኤል ደምሴ በኢትዮጵያ ቡናው ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከኃላፊነት መነሳት ላይ የሰጠውን ምላሽ ከጋዜጣው ያገኙታል፤ ሀትሪክ ከዛ ውጪም በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአንድ ዓመት ቅጣት ተጥሎበት የነበረው ብሩክ ቃልቦሬ ቅጣቱን መጨረሱን ተከትሎ ለአዳማ ከነማ ፊርማውን ስለማኖሩ እንደዚሁም ያለፈውን አንድ ዓመት በምን መልኩ እንዳሳለፈ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች ያቀረብንለት ሲሆን ተጨዋቹ ለሁሉም ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ከዛ ውጪም መከላከያ እና ኢትዮጵያ ቡና በሚያደርጉት የነገው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ዙሪያ የመከላከያው ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩ/ ጨዋታውን አስመልክቶ የሚላችሁ አለ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋም ነገ እና ከነገ ወዲያ የሚካሄዱትን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድርን አስመልክቶ እና በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታላላቅ ጨዋታዎች ዙሪያ ስለ ማንቸስተር ዩናይትዱ ልዩነት ፈጣሪ ተጨዋች ፖል ፖግባ አርሰናልን ወደ መረጋጋት ስለመለሰው ላካዜት እና ሊቨርፑልን ወደ ድል ስለመለሰው ስኬታማው ተጨዋች መሐመድ ሳላና ሌሎችም ያልተሰሙ ሰፋ ያለ መረጃን በነገው እትም አቅርቦሎታለች፡፡
ሀትሪክ የእርሶ ናት፤ አታምልጦት
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
አስተያየት ይስጡ