የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለትግራይ ክልል ክለቦች ተጨዋቾች የሰጠው የዝውውር ቀነ ገደብ ሊጠናቅቅ ሰአታት በቀረበት በአሁኑ ወቅት የመቀለ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ ወደ ወልቂጤ ከተማ ማቅናተ ታውቋል።
ተጨዋቹ በበርካታ ክለቦች ቢፈለግም ሳይሳካ
ቀርቶ የተጨዋቹ ቆይታ የደግአረገ ይግዛው ወልቂጤ ከተማ ሆኗል። በዚሁ ቀነ ገደብ ለመጠቀም ዮናስ አላባም ወድ ሀዲያ ሆሳዕና ለመዛወር ከጫፍ መድረሱ ታውቋል።
ፌዴሬሽኑ ካላራዘመው በስተቀር ልዩ የዝውውር መስኮቱ ዛሬ 11 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ