ታላቁ ሩጫ የሴቶች ውድድሩን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ

ዛሬ ረፋድ ላይ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመታዊ የሶፊ ማልት ቅድሚያ ለሴቶች የ አምስት ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ። ” የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት እናክብር ” በሚል መርህ በርካታ ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ እና ከ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጥንቃቄ ጋር የተካሄደው ይህ ውድድር ለአሸናፊዎች ዳጎስ ያለ ሽልማትን አበርክቷል ።

በእለቱ ታላላቅ የክብር እንግዶችን ጨምሮ ታላላቅ አትሌቶች መሰረት ደፋር ፣ ሰንበሬ ተፈሪ የመሳሰሉ አትሌቶች በስፍራው ተገኝተዋል ።

ለ አስራ ስምንተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ውድድር በአዋቂ አትሌቶች ውድድር አትሌት ፋንታዬ ቀዳሚው ቦታ በመያዝ የ ሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማትን ማግኘት ችላለች ።

በ ውድድር ላይ አሸናፊዎች የገንዘብ ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ።

1ኛ ፋንታዬ በላይነህ :- የ 50,000 ብር ሽልማት እና አንድ አመት የጂም አገልግሎት እና የስፓ ከሀያት ሪጀንሲ

2 ኛ መድን ገ/ስላሴ :- የስድስት ወር የጂም አገልግሎት በ ሀያት ሪጀንሲ ሆቴል

3ኛ ፍታው ዘርአይ :- የሶስት ወር የጂም አገልግሎት በተመሳሳይ ከ ሀያት ሪጀንሲ በነፃ እንደሚያገኙ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ተገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor