አበባው ሰለሞንና ወልቂጤ ከተማ ሊለያዩ?

ከከፍተኛ ሊግ እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው ወልቂጤ ከተማ ከፕሬዝዳንቱ አበባው ሰለሞን ጋር ሊለያይ መሆኑ ተሰምቷል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ፕሬዝዳንቱ ራሳቸውን ማግለላቸውንና በቃኝ ያሉበትን ደብዳቤ ለክለቡ ከሳምንታት በፊት ማስገባታቸው ተረጋግጧል።
በጉዳዩ ላይ ለማናገር ወደ አቶ አበባው ሰለሞን የግል ስልክ ደጋግመን ብንደውልም ማግኘት አልቻልንም ያም ሆኖ ግን አቶ አበባው ከክለቡ አሰልጣኞች ጋር መደዋወል እንዳቆሙ ሲደወልላቸውም እንደማያነሱ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *