ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በ አስራ ሁለተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ አንድ ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ።
የ ቅዱስ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በዚህኛው ሳምንት ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚው ተጫዋቾች ናቸው ።

በአስራ ሁለተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሰላሳ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 310 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በ አስራ ሁለተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የወልቂጤ ከተማው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው እና የወላይታ ድቻው በረከት ወልዴ የቀይ ካርድ የተመለከቱ  ተጫዋቾች ናቸው ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ የካቲት 15 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

1. በረከት ወልዴ (ወላይታ ድቻ) አርብ የካቲት ቋ12 2013 ዓ ም ክለቡ ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ12ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ የማግባት ዕድል በማበላሸት ሪፖርት ቀርቦበታል። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3,000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ወስኗል።

2. ጅማ አባ ጅፋር ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ የ ቡድኑ ተጫዋቾች ውብሸት አለማየሁ ፣ አብርሀም ታምራት ፣ ኤልያስ አታሮ ፣ ሙሉቀን ታሪኩ እና አቡበከር ኑሪ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተላልፎባቸዋል ።

3.ወልቂጤ ከተማ ከ ሰበታ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ የቡድኑ ተጫዋች የሆኑት ቶማስ ስምረቱ ፣ ይበልጣል ሽባባው እና ጀማል ጣሰው ( ሁለት ጊዜ ) በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተላልፎባቸዋል ።

4. የፋሲል ከተማው ተጫዋች አምሳሉ ጥላሁን በአምስት ጨዋታዎች ላይ የቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ አንድ ጨዋታ እንዲቀጣ እና 1,500 የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍል ተወሰኖበታል ።

5. ጀማል ጣሰው (ወልቂጤ ከተማ ) ክለቡ ከሰበታ ከተማ ጋር ባደረገው የ12ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ካለቀ በኋላ የዕለቱን ዳኞች አፀያፊ ስድብ መሳደቡ ከዋና ዳኛውና ከ ጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3,000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ወስኗል ።

6. በሲዳማ ቡና እና በሃዲያ ሆሳዕና መካከል አርብ ታህሳስ 16 2013 በ3ኛው ሳምንት በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡና እግር ኳስክለብ በሃዲያ ሆሳዕና በኩል ተሰልፈው በተጫውቱት የውጭ አገር ዜጋ ተጫዋቾች ዙሪያ የተገቢነት ክስ በማቅረቡ በዕለቱ የተገኘው ውጤት አለመፅደቁ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበርና ሊግ ኮሚቴ የተጫዋቾችን ምዝገባ ለሚያካሂደው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንበቀረበው የተጫዋቾቹ ተገቢነት ክስ ላይ ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ በደብዳቤና በቃል ጥረት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በኩል ምላሽ ሊገኝ ስላልተቻለና ጥያቄውን ላቀረበውም ሆን ክስ ለቀረበበት ክለብ ውሳኔው ከዚሀ በላይመዘግየት የሌለበት መሆኑን በማመን ውሳኔው ባለው መረጃ መሰረት በሊግ ኮሚቴው ወሳኔ እንዲሰጥበት ተወስኗል።በመሆኑም

1. የተጫዋቾችን መረጃ አጣርቶ ቲሴራ ካርድ/መታውቂያ / የሚሰጠው ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን መሆኑን ታሳቢ በማድረግ

2.ክስ የቀረበባቸው ተጫዋቾች በሙሉ ጨዋታ ከማድረጋቸው በፊት በጨዋታ አመራሮች በኩል ህጋዊ ቲሴራ/ከፌዴሬሽኑ ሀጋዊማህተም እና አግባብ ባለው ሃላፊ ተፈርሞበት የመጣ ቲሴራ መያዛቸው በመረጋገጡየሲዳማ ቡና ያቀረበውን የተጫዋቾች ተገቢነት ጥያቄ ውደቅ በማድረግ በዕለቱ የተመዝገበው ውጤት ሲዳማ ቡና ከ ሃዲያሆሳዕና(1-3) እንዲፀድቅ ሊግ ኮሚቴው ወስኗል።

ጥሪ

ለባህርዳር ከተማ፣ ሃዋሳ ከተማ እና ለፋሲል ከነማ የቡድን መሪዎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የባህርዳር ውድድር አመራርና ስነስርዓትኮሚቴ ሊያነጋግራችሁ ስለሚፈልግ ማክሰኞ የካቲት 16 2013 በባህርዳር ስታድየም ከቀኑ በ9 ሰዓት እንድተገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል ።

የአስራ ሶስተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጰያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በነገው ዕለት በተጠባቂ መርሀ ግብሮች በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *