“ራሴን ስለምጠብቅ፤ ለኳሱ ትልቅ ፍቅር ስላለኝ እና የተሰጠኝን ስራ በአግባቡ ስለምጠቀም በጥሩ ደረጃ ላይ ልገኝ ችያለሁ”ሽመልስ በቀለ /ምስር አል-ማቅሳ/

“ራሴን ስለምጠብቅ፤ ለኳሱ ትልቅ ፍቅር ስላለኝ እና የተሰጠኝን ስራ በአግባቡ ስለምጠቀም በጥሩ ደረጃ ላይ ልገኝ ችያለሁ”

“በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ምርጥ ተጨዋቾች አሉ ነጥዬ ላውጣ ብል መርጬ አልጨርሳቸውም” ሽመልስ በቀለ /ምስር አል-ማቅሳ/

 

ከሀገራችን የደቡቡ ክፍል ውቢቷ ሀዋሳ በ ሀዋሳ ከተማ አንድ ብሎ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ሽመልስ በቀለ በሰሜን አፍሪካዊቷ ግብፅ ከትሞ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል ።

በግብፅ የተሳኩ አመታትን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የመሀል ሜዳው ቴክኒሺያን ሽመልስ በቀለ ዘንድሮ ላይም የቀደመ ብቃቱን ሲያሳይ ከወዲሁ የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ይገኛል ።

በግብፅ የመገናኛ ብዙሀን ጨምሮ በታላላቆቹ የሀገሪቱ ሀያላን ክለቦች ታላለቅ ተጫዋቾች እየተሞካሸ ይገኛል ።

የቀድሞው የአል አህሊ ተጫዋች እና በአሁን ሰዓት በግብፅ የመገናኛ ብዙህን ቴሌቪዥን የግብፅ ኳስን በመተንተን የሚታወቀው ሀዚም ኢማም የዋልያዎቹን ኮከብ ሽመልስ በቀለ ከ ማንችስተር ሲቲው ራሂም ስተርሊንግ ጋር ሲያወዳድረው በይፋ ተሰምቷል ።

የዋልያዎቹ ኮከብ ሽመልስ በቀለ በወቅታዊ ብቃቱ ፣ ስለ ወደፊት ጉዞው ፣ ስለ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እና ሌሎች ጉዳዮች ከሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ፀሀፊው ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ካለበት ከግብፅ የቀጥታ ቆይታን አድርጓል ።

ሽመልስ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች መውጣት በሚከብዳቸው ሰዓት ወደ ግብፅ አቅንቶ ብቃቱን ማሳየት ችሏል ሚስጥሩ ምንድነው ?

ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ይሄን ያህል ጊዜ እንደዚህ በጥሩ አቋም ልቆይ የቻልኩበት አንደኛው ነገር ራሴን ስለምጠብቅ ቢሆንም ከምንም በላይ ለእግሩ ኳሱ ትልቅ ፍቅር ስላለኝ እና የሚሰጠኝን ስራ በአግባቡ መስራቴ እና የተሰጠኝን እድል መጠቀሜ ነው ። ማንኛውም ተጫዋች አለማ ካለው ትልቅ ቦታ መድረስ የሚፈልግ ከሆነ ያንን ነገር በፍቅር ይዞ ብዙ ቦታ መጓዝ ይችላል ።

ከተጫዋችነት እስክ አምበልነት ቡድንክን መምራት የቻልክባቸው አጋጣሚዎች አሉ እንዴት ትመለከተዋለክ ?

“ያለፍኩባቸው ሰባት አመታት ብዙ ፈተናዎች አጋጥመውኛል ፣ ብዙም ነገሮችም ተምሬ አልፌያለው ። በተለይም በ ፔትሮጀት ለአራት ዓመት ከግማሽ ስቆይ የመጨረሻዎቹን ሁለት ዓመታት ቡድኑን በአምበልነት መምራት ችያለው ። ለእኔ ይሄ ትልቅ ነገር ነው ፣ ምክንያቱም በእግር ኳስ ህይወት ውስጥ ስኬታማ ብዬ ያሳለፍኳቸው ነገሮች አሉ ፤ ከእነዚህ መካከልም ይሄኛው ቀዳሚው ነው ።

ሀገር ውስጥ እያለው ክለቤን በአምበልነት የመምራት እድሉን አላገኝሁትም ነበር እና ከሀገር ወጥቼ ይህን እድል ሳገኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ ። አምበል ስትሆን ብዙ ሀላፊነቶች አሉብክ ፣ ይህንንም እድል በአግባቡ ተጠቅሜበታለው ። ከምንም በላይ እና ከሁሉም አስቀድሞ ግን ሀገሬን በአምበልነት የመራሁበት ጨዋታ በእግር ኳስ ህይወቴ ትልቅ ነገር ያየሁበት እና የተደሰትኩበት ነው ።”

የ ግብፅ ቆይታክን በስፋት እንዴት ትገልፀዋለክ ?

“በ ግብፅ ቆይታዬ በጣም ብዙ ነገሮችን አይቻለው ብዙ ፈተናዎችንም አልፌያለው ፣ ከምንም በላይ ግን በጣምም ደስተኛ ነኝ ። በእግር ኳስ ህይወቴ ውስጥ ለእኔ እንደ ፕሮፌሽናልነት ትልቅ ቦታ ያየሁበት ነው ። ከምንም በላይ ደግሞ በየአመቱ የተማርኩበት እና በተለያዩ አሰልጣኞች መሰልጠን መቻሌ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው ።

በልጅነቴ ቁጭ ብዬ የአፍሪካ ዋንጫን በ ቴሌቪዥን መስኮት ስመለከት የማያቸውን የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እንደ ሚዶ ፣ ሞሐመድ ሀሰን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ብዙዎቹ አሰልጥነውኝ አይቻለው እና ያንን እድሉን በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ።”

በሰኬት ስለታጀበው የዘንድሮው የውድድር ዓመቱ ?

የዘንድሮው የውድድር ዓመት በጣም የሚያስገርም እና የሚያስደንቅ ደስ የሚል ብቃት ያሳየንበት ነው ። ክለቡም ሆነ ያሉት ተጫዋቾች ጥሩ ናቸው ፣ እኔም በግሌ የማደርገው ከፍተኛ ተፅዕኖ አል መካሳን አሁን ላይ ላለው ሁለተኛ ደረጃ አብቅቶታል ።
ወደ ጎል በመቅረብ ባደረግናቸው አስራ አራት ጨዋታዎች ስድስት ጎሎችን አስቆጥሬ አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቼ ማቀበል ችያለው ።

ለእኔ ይህ ትልቅ ነገር ነው ፣ አል መካሳን ከተቀላቀልኩ አመት ጀምሮ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ደስተኛ እያደረገኝ ያለው ጊዜ ነው ። ወደ ፊት ብዙ ሊፈጠሩ የሚችሉ ነገሮች ቢኖሩም ከስራዬ ጋር የሚታዪ ቢሆንም በዚሁ የምቀጥል ከሆነ የተሻለ ነገር እሰራለው ብዬ አስባለው ።

ስለ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እና ምርጥ ተጫዋች ?

“የዘንድሮውን የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እከታተላው ፣ ምክንያቱም ከልምምድ በኋላ ረጅም ጊዜን በመኖሪያ ቤቴ ስለማሳልፍ የማየት እድሉን በሰፊው ፈጥሮልኛል ። በጣም ደስ የሚሉ እና ካለፉት አመታት የተሻሉ ነገሮችን ለመመልከት ችያለው ። ውድድሩ በቴሌቪዥን መተላለፉ እግር ኳሳችን ትልቅ ሲያደርገው ለተጫዋቾች መልካም አጋጣሚ ነው ።

በኢትዮጵያ ብዙ ምርጥ ተጫዋቾች አሉ ፣ ሁሉም ምርጦቼ ናቸው ። አንድ ተጫዋች ነጥዬ ላውጣ ብል መርጪ አልጨርሳቸውም ፣ በጣም ኳስ የሚችሉ ብዙ ተጫዋቾች አሉ ።”

ሽመልስ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ያለፋቸው ውጣ ውረዶች ምን ይመስሉ ነበር ?

“እውነት ለመናገር ከሆነ ብዙ ፈተናዎች እና ውጣ ውረዶች አሉት ፣ ኢትዮጵያ ሆነ እኔ እዚህ የምስራውን ማየት ቀላል ይመስል ይሆናል ።

ከሀገር ውጪ ፕሮፌሽናል ሆኖ መጫወት ብዙ ችግሮች አሉት ፣ አውሮፓ ውስጥ ቢሆን ብዙ ነገሮች ሰለሚሟሉ ቀላል ይሆን ነበር ። እዚህ ብዙ ፈተናዎችን አልፌ በእንደዚህ ስኬታማ ጉዞ መቀጠሌ በጣም ደስተኛ ነኝ ። ምክንያቱም በጣም ትዕግስተኛ ነኝ ፣ ይህ ትዕግስተኛነቴ ደግሞ ጠንከራ እንድሆን አድርጎኛል ።”

ሽመልስ በቀጣይ አመታት ምን ያስባል ?

አሁን ላይ ስለቀጣይ አመታት ማሰብ ይከብደኛል ፣ ምክንያቱም አሁን ያለሁበት ቦታ ስለሚቀጥለው የሚያሳስበኝ ፣ ዛሬ ጥሩ ነገር ከሰራው ለሚቀጥለው የተሻለ ነገር አገኛለው ብዬ አስባለው ።ሁሉንም ነገር የሰጠኝ ፈጣሪ ነው ፣ በሰጠኝ ነገር ልቀልድበት አልችልም ። ክህሎቱን እግዚአብሔር ይመስገን ሰጥቶኛል ፣ ያንን ነገር በአግባቡ ነው የምጠቀምበት ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *