ላለፉት ሶስት ቀናቶች ልምምድ አቁመው የነበሩት ወልቂጤ ከነማዎች ዛሬ ልምምዳቸውን ጀመሩ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከአንድ ዓመት በፊት የተቀላቀሉት ወልቂጤ ከተማዎች ለተጨዋቾቻቸው የፊርማ እና የሶስት ወር ወርሃዊ ክፍያን ካለመፈፀም ጋር በተያያዘ ተጨዋቾቹ ላለፉት ሶስት ቀናት ልምምድን አቁመው የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን የቡድኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ የፊርማውን ክፍያ እና በ2 ቀን ጊዜ ውስጥ ደግሞ የወርሃዊው ክፍያው በእርግጠኝነት ይፈፀምላችኋል በሚል ቃል ስለተገባላቸው ልምምዳቸውን ጀምረዋል።

ክትፎዎቹ በሚል ቅፅል ስም ለሚታወቁት ለእዚህ ቡድን ተጨዋቾችም በተባለው ጊዜ ይሄን ክፍያ ምንአልባት ቡድኑ ባይፈፅም እንኳን የቡድኑ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው ለክለባቸው ባላቸው ልዩ ፍቅር ከራሳቸው ኪስ ለተጨዋቾቹ ደመወዙን በመክፈል ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡና ይህን ቃልም ከእሳቸው አንደበት ተጨዋቾቹ በመስማታቸውም አቶ አበባው ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸውም ተጨዋቾቹ እየገለፁ ይገኛል።

የወልቂጤ ከተማው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው በዚህ ቡድን የእስከአሁን ቆይታቸው ለክለቡ ከሚያደርጉት በጎ ነገር በመነሳት በቡድኑ ተጨዋቾች በየጊዜው የሚወደዱና የሚመሰገኑ ሲሆኑ ለኳስ ያላቸው ከፍተኛ ፍቅርም እየተነገረላቸው ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወልቂጤ ከነማዎች በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ላይ በሚጀመረው ውድድር ዐርብ 10 ሰዓት ላይ ባህርዳርን እንደሚገጥሙ ታውቋል።

Editor at Hatricksport website

Facebook

መሸሻ ወልዴ

Editor at Hatricksport website

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *