ክትፎዎቹ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠሩ

በቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሰመረ ጅማሮን በ አሰልጣኝ ደግ አረገ ይግዛው ማድረግ የቻሉት ወልቂጤ ከተማዎች አዲስ አሰልጣኝ መቅጠራቸው ተገልጿል ።

በተጠናቀቀው የባለፈው የውድድር ዓመት ስሑል ሽረን ተረክበው የነበሩት አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ ቀጣዩ የወልቂጤ ከተማ ሆነው መሾማቸው ለማወቅ ተችሏል ።

አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀ ከዚህ ቀደም ሼር ኢትዮጵያ፣አክሱም ከተማ፣ሰበታ ከተማ፣አዳማ ከተማ እና ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በረዳትነት ማሰልጠን ችለዋል ።

ወልቂጤ ከተማ በ ሀያ አንድ ነጥብ አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ በተለይም ላለመውረድ ከ ድሬደዋ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ በጉጉት የሚጠበቅ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor