ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ እሁድ ግንቦት 1 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።

1. ላሚን ኩማረ (አዳማ ከተማ) ከ ድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ 22 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በ79 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ወስኗል።

2. አዳማ ከተማ ክለቡ ከ ድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ 22 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የ አዳማ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት አሊሲ ኦቢሳ ጆናታን ፣ ላሚን ኩማረ ፣አሚኑ ነስሩ ፣ ላሚን ኩማረ ፣ ሳኮባ ካማራ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

3. ከድር ኩሊባሊ(ፋሲል ከነማ) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

4. በረከት ወልዴ(ወላይታ ድቻ) በተመሳሳይ አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

ጥሪ

ለሃዲያ ሆሳዕና ክለብ ስራ አስኪያጅ ፣ ለ ባህር ዳር ከተማ የቡድን መሪና ረዳት አሰልጣኝ አብርሃም መላኩ የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት
ኮሚቴ ሊያነጋግራችሁ ስለሚፈልግ ሰኞ ግንቦት 2 /2013 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ስቴዲየም እንድተገኙ ጥሪ ተላልፏላቸዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor