ወልቂጤ ከተማ በዲሲፕሊን ጥሰት 3 ተጨዋቾቹን አገደ

ወልቂጤ ከተማ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ጥሰዋል ያላቸውን ሶስት ተጨዋቾቹን በጊዜያዊነት አገደ።

ከክለቡ በተገኘ መረጃ ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩ/፣ ይበልጣል ሽባባውና አዳነ በላይነህ ወልቂጤ ከተማ በፋሲል ከነማ 1 ለ 0 በተሽነፈበት ምሽት ፕሮቶኮሉን ጥሰው ከሆቴሉ መውጣታቸውን ተከትሎ ክለቡ በጊዜያዊነት አግዷቸዋል።

ወልቂጤ ከተማ ውጤት ባጣበትና በተቸገረበት ጊዜ ፕሮቶኮሉን ጥሰው ለመዝናናት መውጣታቸው የክለቡን አመራሮች አስቆጥቷል።በዚህም መሰረት የክለቡ ቦርድ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በጊዜያዊነት መታገዳቸው ታውቋል። ይህም ወልቂጤ ከተማን በዲሲፕሊን ጥሰት ተጨዋቾቹን የቀጣ ሶስተኛው ክለብ አድርጎታል።

በሌላ በኩል ወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃምን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል። አሰልጣኝ ደግአደረገ ከድሬዳዋው ውድድር ጀምሮ በህመም መለየቱን ተከትሎ አሰልጣኝ ሲሳይን ቀጥሮ አሰልጣኙ ስራውን ዛሬ ጀምሯል።
ቀጣይ የውል ሂደቶቹ ወደፊት የሚገለጽ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport