መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጌታነህ ከበደን አላሰለፉም የተባሉት የወልቂጤ ከተማ ቡድን መሪ ታገዱ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ጌታነህ ከበደን አላሰለፉም የተባሉት የወልቂጤ ከተማ ቡድን መሪ ታገዱ

አጋራ
አጋራ

“በቀጣዩ ጨዋታ ጌታነህን እናሰልፈዋለን”
አቶ ብርሃኑ በጋሻው /የተጨዋቹ ጠበቃ/

ወልቂጤ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ እንዲሰለፍ መመርያ የተሰጣቸው የቡድን መሪው አወል ከድር ሃላፊነታቸውም አልተወጡም በሚል መታገዳቸው ተሰማ።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ጌታነህ ከበደ ቅጣቱ ተነስቶለት እንዲጫወት ቢወስንም የሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ አልቀበልም በማለቱ ጌታነህ ከበደ በዛሬው ጨዋታ ሳይሰለፍ የቀረ መሆኑ ይታወቃል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተገኘውን መረጃ ያረጋገጡት የጌታነህ ከበደ ጠበቃ የህግ ባለሙያው ብርሃኑ በጋሻው ግን በጨዋታው ጌታነህ እንዲሰለፍ ክለቡ ወስኖ ለሊግ ኩባንያው ገልጾ እያለ ቡድን መሪው አወል ከድር የተወሰነውን ውሳኔ በመተግበር ጌታነህ ከበደን እንዲገባ አላደረጉም በሚል ከደመወዝና ከስራ መታገዳቸውን አስረድተዋል።

ጠበቃው አክለው እንደገለጹት አሁንም የሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ውሳኔን እንደማይቀበሉትና የፊታችን ሀሙስ ሰኔ 16/2014 ከቀኑ 7 ሰዓት ከሲዳማ ቡና ጋር በሚደረገው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ እንደሚሰለፍ ተናግረዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...