አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ወላይታ ድቻን ለቀጣይ አንድ አመት በዋና አሰልጣኝ ለመምራት ተሹሟል።
አመቱን በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ቢመራም የኋላ ኋላ ያሰናበተው በቀጣይ ጨዋታዎችም ደግሞ በቴዎድሮስ ቀነኒ እና አምጣቸው ሀይሌ የተመራው ወላይታ ድቻ በአመቱ አራተኛ አሰልጣኙ በማድረግ የቀድሞው አሰልጣኙ መሳይ ተፈሪን በአንድ አመት ውል ሾሟል። ክለቡን ከታችኛው ሊግ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደረጉት እና ወደ አርባምንጭ ከተማ በማምራትም ቡድኑን አሳድገው በፕሪምየር ሊጉ የመሩት አሰልጣኙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን በምክትል እና በዋና አሰልጣኝነት ካገለገሉ በኋላ ወደ ቀደመ ቡድናቸው መመለስ ችለዋል።
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የራሱን ረዳት አሰልጣኞችን እንዲያመጣ እና ወላይታ ድቻን በፕሪሚየር ሊጉ ማቆየት ደግሞ እንደ ግዴታ ተቀምጦለታል።



